መቀመጫቸውን ለማስተለቅ የሚታትሩ ሴቶች እየሞቱ ነው

ይህቺ ሴት ለቢቢሲ እንደተናገረችው ሕመሙ ከ2 ዓመት በኋላም አልጠፋም

በሺህ የሚቆጠሩ ሴቶች መቀመጫቸውን ሞንዳላ ለማድረግ ሰማይ ይቧጥጣሉ። የብሪታኒያ የፕላስቲክ ሰርጀሪ ማኅበር እንዳለው ይህ መቀመጫን የማደለብ ቀዶ ጥገና ሕክምና ገዳይ እየሆነ መጥቷል።

በዚህ ሳምንት ሁለተኛዋ ብሪታናዊት ሴት ይህንኑ “የብራዚል መቀመጫ” በሚል የሚቆላመጠውን አደገኛ የቀዶ ሕክምና በማድረግ ላይ ሳለች ሕይወቷ አልፏል።

ዳሌንና መቀመጫ የማሞናደሉ ተግባር በተለይ በሆሊውድ ሴቶች የተለመደ ነው።

ሆኖም ሌሎች የሆሊውድ ዕውቅ ሴቶችን በማየት ብቻ ደረጃውን ያልጠበቀ የሕክምና ማዕከላትን ይጎበኛሉ።

የብሪታኒያ የቁንጅና ቀዶ ጥገና ማኅበር ያወጣው ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ ከ3ሺህ ሴቶች አንዷ በዚሁ መቀመጫን የማሞናደል የቀዶ ጥገና ሕክምና ምክንያት ሕይወቷን ታጣለች።

ይህ ሕክምና በተለምዶ ቢቢኤል ወይም (Brazilian butt lift (BBL)) በመባል ይታወቃል። ሂደቱም ስብ ካለው ማንኛውም የሰውነት ክፍል ሥጋ ቦጨቅ አድርጎ ወስዶ መቀመጫ ላይ የመለጣጠፍ ሂደት ነው።

ሴቶቹ ለሞት የሚዳረጉት ከሌላ የሰውነት ክፍል ተቦድሶ የሚመጣው የደለበ ሥጋ መቀመጫ ላይ በሚለጠፍበት ጊዜ የደም ዝውውርን ስለሚገታ ነው።

የ23 ዓመቷ የዌልስ ነዋሪ ለቢቢሲ እንደተናገረችው ይህንን የቀዶ ጥገና ሕክምና ካደረገች በኋላ ለከፋ የጤና መስቅልቅል ተጋልጣለች።

“አሁን እኮ በትክክል እንኳ መራመድ ተስኖኛል” ትላለች።

ኪም ካርዳሺያንን የመሰሉ እውቅ ሴቶች ሞንዳላ መቀመጫ በማሰራት ይታወቃሉImage copyright: Getty IMAGES
አጭር የምስል መግለጫኪም ካርዳሺያንን የመሰሉ እውቅ ሴቶች ሞንዳላ መቀመጫ በማሰራት ይታወቃሉ

ይቺ ወጣት ጨምራ እንደተናገረችው “መጀመርያ አካባቢ መቀመጫዬ እርጥበት ማመንጨት ጀምሮ ነበር። ይህም ልብሴን ያበሰብሰው ጀመረ” ብላለች።

“ሽታ አለው፤ አስቀያሚ ነገር ነው የሆንኩት፤ ገንዘቤን ባልረባ ነገር በተንኩኝ፤ ጤናዬን አጣሁ፤ የተፈጥሮ ሰውነቴን እወደው ነበር” ስትል በውሳኔዋ መጸጸቷን ተናግራለች።

ይህን መቀመጫ የማደለብ ቀዶ ጥገና ሕክምና ለማግኘት በአማካይ 13ሺህ ዶላር (358ሺህ ብር ገደማ) ያስፈልጋል። እስከ 20 ቀናት የሆስፒታል አልጋን መያዝም ይጠይቃል።

ስሟን መግለጽ የማትፈልግ ሌላ ሴት ለቢቢሲ እንደተናገረችው ይህንኑ መቀመጫን የማሞንደል ሕልሟን ለማሳካት የሄደቸው ወደ ቱርክ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ “ዋጋው ከእንግሊዝ በጣም ያነሰ ነበር”።

ሐኪሟን ያየችው ግን ቀዶ ጥገናውን ለማድረግ ማደንዘዣ ከመውሰዷ ከ10 ደቂቃ በፊት ነበር።

መቀመጫን የማደለብ ቀዶ ጥገናImage copyrightGETTY IMAGES

ከቀናት በኋላ ኃይለኛ ትኩሳት እንደጀመራትና ነርሶችንና ሐኪሞችን ለማናገር ስትሞክር ቸል እንዳሏት አስታውሳለች። ሕመሙ ግን አሁንም ከሁለት ዓመት በኋላ እየተሰማት እንደሆነ አምናለች።

50 ከመቶ የሚሆኑት መቀመጫ አሞንዳይ ሴቶች ወደ ቱርክ እንደሚያቀኑና ቀሪዎቹ ደግሞ ሀንጋሪ፣ ቤልጂየምና ስፔንን መዳረሻ እንዳደረጉ ተመልክቷል።

በነዚህ አገራት ርካሽ ቀዶ ጥገናን የሚያደርጉ ሴቶች ከሕክምና በፊት አስገዳጅ ውል እንዲፈርሙ እንደሚደረግና ሕክምናውን በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያጥላሉ ከሆነ በስም ማጥፋት ክስ እንደሚጠብቃቸው ይስማማሉ።

ምንጭ: BBC

Advertisement

13 Comments

  1. I抦 impressed, I must say. Actually not often do I encounter a weblog that抯 both educative and entertaining, and let me inform you, you might have hit the nail on the head. Your concept is excellent; the difficulty is something that not sufficient people are talking intelligently about. I’m very comfortable that I stumbled throughout this in my seek for one thing referring to this.

  2. I抎 must test with you here. Which is not something I often do! I take pleasure in studying a put up that can make people think. Also, thanks for permitting me to remark!

  3. Youre so cool! I dont suppose Ive learn something like this before. So good to search out somebody with some original ideas on this subject. realy thanks for starting this up. this web site is something that’s needed on the net, somebody with a bit of originality. useful job for bringing something new to the web!

  4. Youre so cool! I dont suppose Ive learn something like this before. So good to search out someone with some authentic ideas on this subject. realy thanks for beginning this up. this web site is something that’s needed on the internet, somebody with just a little originality. helpful job for bringing one thing new to the web!

Comments are closed.