የጥርሳችንን ጤና መጠበቅ ለአጠቃላይ ጤናችን ያለው ፋይዳ

Healthy woman teeth and a dentist mouth mirror

የጥርስን ጤንነት መጠበቅ ፈገግታን ከማሳመር በላይ ስለ አጠቃላይ የጤንነታችን ሁኔታ የሚለን ነገር አለ ይላሉ ተመራማሪዎች።

በአጠቃላይ የአፋችንን ጤንነት በተለይ የጥርስን ጤንነት አጠቃላይ ጤናችን ምን ይመስላል የሚለውን ለመለየት እንዴት ይጠቅማል በሚለው ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶች ሲሰሩ ቆይተዋል።

ከዚህ በፊት ከተሰሩ ጥናቶች ውስጥም አንዳንድ የጥርስ ህመሞች ለስኳር በሽታ መጋለጣችንን ምልክት የሚሰጡ መሆኑ ተጠቅሷል።

የተወሰኑ የጥርስ ህመሞች ደግሞ ለስትሮክ (ወደ አእምሯችን የሚገባው ደም መቋረጥ ወይም መቀነስ) የጤና ችግር ተጋላጭነት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅት እየተሰራ ያለው ጥናት ደግሞ ከእድሜያችን ጋር ተያይዞ ጥርሳችን ያለብት ሁኔታ ከልብ ጤንነት ጋር ምን አይነት ግንኙነት አለው በሚለው ላይ የሚያጠነጥን ነው።

የአሜሪካ ኒው ኦርሊያንስ ቱላን ዩኒቨርሲቲ እና በቦስተን ሀርቫርድ ቲ.ኤች ቻን የህብረተሰን ጤና ትምህርት ቤት በጋራ እያካሄዱት ያለው ጥናት በመካከለኛው የእድሜ ክልል የሚከሰት የጥርስ መነቀል እና መሰባበር ላይ ያተኮረ ነው።

በጥናቱ ላይ እድሜያቸው ከ45 እስከ 69 መካከል የሚገኙ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን፥ ጥርሳቸው መነቀል አለመነቀሉ እንዲሁም ከተነቀለ ደግሞ በስንት ዓመት ልዩነት የሚለው ላይ ክተትል አድርጓል።

በተሳታፊዎች ላይ ክትትል መደረግ ከተጀመረ በኋላም ከተሳታፊዎቹ ውስጥ በ8 ዓመት ውስጥ አንድ ጥርስ እንደተነቀለባቸው አስታውቀዋል።

ጥናቱ ከተጀመረ ከ12 እስከ 18 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ አንድ እና ሁለት ጥርስ የተነቀለባቸው ተሳታፊዎች እንዳሉ ነው አጥኚዎቹ የገለፁት።

ተመራማሪዎቹ ባደረጉት ክተተልም በመካከለኛው የእድሜ ክልል ውስጥ ሁለት እና ከዚያ በላይ ጥርሳቸው የተነቀለባቸው ሰዎች ከከፍተኛ የልብ ህመም ተጋላጭነት ጋር ግንኙነት እንዳለው ለይተዋል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.