ጥቂት ስለ ማህፀን ጫፍ ላይ ካንሰር – What is Cervical Cancer?

በአለማችን በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች የቀዳሚነት ደረጃ የሚይዘው የማህፀን ጫፍ ላይ ካንሰር በመባል ይታወቃል።

በአብዛኛው ወጣት ሴቶችን የሚያጠቃውና እንደ ኢትዮጲያ ያሉ ታዳጊ ሀገሮች ላይ የሚበረክተው ይህ የካንሰር አይነት ከሚያጋልጡ ሁኔታወች ውስጥ በጥቂቱ

1. ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ በመባል የሚታወቅ የቫይረስ አይነት
2. ከአንድ በላይ ሰዎች ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ
3. ከሀያ ዓመት እድሜ በታች የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት
4. የአባላዘር በሽታዎች
5. በኤች አይ ቪ ቫይረስ የተጠቁ

ከበሽታው ምልክቶች በጥቂቱ?

1. ለየት ያለ በማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ
2. ያለወትሮ በማህፀን የደም መፍሰስ
3. ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኃላ የሚከሰት የደም መፍሰስ ናችው

እነዚህ ምልክቶች ከታዮዎት በአፋጣኝ ወደ ጤና ማዕከል በመሄድ ተገቢውን ምርመራ ማድረግ ይገባል።

የማህፀን ጫፍ ላይ ካንሰርን ለመከላከል

1. በሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ የመጠቃት ዕድልዎን ጥንቃቄ የተሞላበት የግብረ ስጋ ግንኙነት በማድረግ ይቀንሱ። ነገር ግን ኮንዶምን መጠቀም ሙሉ በሙሉ ለቫይረሱ ተጋላጭነትን አይቀንስም።

2. ሲጋራ የሚያጤሱ ከሆነ እንዲያቆሙ ይመከራል

3. ቅድመ ካንሰር ምርመራዎችን ማድረግ ዋንኛው የመከላከያ መንገድ ሲሆን ፓፕስ ሚር(Pap smear) የሚባል የምርመራ አይነትን በመደበኛ ሁኔታ ማድረግ ህመሙ ወደ አድገኛ ደረጃ ሳይደርስ መቆጣጠር ይቻላል። ምርመራውን ማንኛውም 21 ዓመት የሞላት ሴት ብታደርግ ይመከራል።

ጤና ይስጥልኝ  Read more at Dr Honeliat Ephrems website

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.