ዘመናዊ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ለረጂም ጊዜ መጠቀም በልጆች አስተዳደግ ላይ አሉታዊ ተጽህኖ አለው

ዘመናዊ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ለረጂም ጊዜ መጠቀም በልጆች አስተዳደግ ላይ አሉታዊ ተጽህኖ እንዳለው አንድ ጥናት አመለከተ።

በዚህም ምዕራብአዊያን ወላጆች ለልጆቻቸው መስጠት የሚገባቸውን ጊዜ የማይሰጠኑና የልጆቻቸውን ሰዕብና በመቅረጽ በኩል መወጣት ያለባቸውን ሚና ሳይወጡ እንደሚቀሩ ነው ጥናቱ ያመላከተው።
ረጂም ጊዜ ስማርት ስልኮቻቸውንና ቴሌቪዥን በመመልከት ለልጆቻቸው ትኩረት ከማይሰጡ ቤተሰቦች የሚገኙ የሚገኙ ልጆች ስነ ልቦና የተዛባ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።
ወላጆቹ በልጆች የምግብ፣ ጨዋታና የመኝታ ጊዜ ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ፋንታ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ ጊዜ የሚያጠፉ መሆኑን ነው ጥናቱ ያመላከተው።
በዚህም ህፃናቱ ነገሮችን ለመሞከር የሚያመነቱ/ፈሪዎች/፣ ቀዥቃዣ፣ ነጭናጫ፣ ዝምተኛ ወይንም ቁጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው የተገለጸው።
በሚችጋን የጤና ትመህርት ክፍል በ172 ቤተሰቦች ላይ በተደረገ ጥናት ወላጆች ቴሌቪዥን፣ ኮምፒዩተር፣ ታብሌትና ስማርት ስልኮቻቸውን በመጠቀም በአማካይ በቀን 9 ሰዓት እንደሚያሳልፉም ተገለጿል።
ከሚባክነው ጊዜ አንድ ሶስተኛ ያህሉም ከእጅ ስልካቸው ጋር እንደሚያባክኑትም ነው ጥናቱ የሚያመላክተው።
የዘርፉ ቴክኖሎጂ በፍጥነት እድገት እየሳየ ሲሆን፥ በወላጆችና ልጆች መካከል ለሚኖረው ቤተሰባዊ ግንኙነት መላላት የሚያሳድረው ተጽህኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱም ተገልጿል።  ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.