ቁርጥማት | Arthritis

“አርትራይተስ” የሚለው ቃል “የበገኑ አንጓዎች” የሚል ትርጉም ካላቸው የግሪክኛ ቃላት የተወሰደ ሲሆን ከ100 ከሚበልጡ የተለያዩ የቁርጥማት በሽታ ዓይነቶች ጋር ተዛማጅነት ያለው ነው።* እነዚህ በሽታዎች አንጓዎችን ብቻ ሳይሆን አንጓዎቹን ደግፈው የሚይዙትን ጡንቻዎች፣ አጥንቶች እንዲሁም አጥንትን ከጡንቻና አጥንትን ከአጥንት የሚያገናኙ ጅማቶችን ጭምር ያጠቃሉ። አንዳንድ የአርትራይተስ ዓይነቶች ቆዳን፣ የውስጥ አካል ክፍሎችንና፣ ዓይንን ሳይቀር ሊያጠቁ ይችላሉ። 

አንጓ ዙሪያ ከአደጋ የሚጠብቀውና ደግፎ የሚይዘው በከዳ (capsule) የተባለ ጠንካራ ገለፈት ይገኛል።የአንጓው በከዳ በሲኖቪያል ገለፈት ይሸፈናል። ይህ ገለፈት የሚያሙለጨልጭ ፈሳሽ ያመነጫል። በአንጓው በከዳ ውስጥ የሁለቱ አጥንቶች ጫፍ የመለጠጥ ባሕርይ ባለው ካርትሌጅ የሚባል ህብረህዋስ ይሸፈናል። ይህም አጥንትህ እርስ በርሱ እንዳይፋተግና እንዳይፋጭ ይከላከላል። በተጨማሪም ካርቲሌጅ በአጥንቶችህ ጫፎች መካከል እንደ ትራስ ሆኖ በማገልገል ንዝረትን የሚቀንስ ከመሆኑም ሌላ በአጥንቶችህ ላይ የሚያርፈው ጭነት ለመላ አጥንቶችህ እኩል እንዲዳረስ ያስችላል፡፡
ምልክቶች
– በእንቅስቃሴ እና በቅዝቃዜ ሰዓት የሚባባስ ህመም
– ጠዋት ጠዋት የመገጣጠሚ አከባቢ ያለ የመጨምደድ ስሜት
– የመገጣጠሚያ እብጠት
ህክምና
– አካላዊ እንቅስቃሴና የአኗኗር ለውጥ ማድረግ
– ፊዚካልቴራፒ ወይም ጤናን ለማሻሻል የሚረዱ የሰውነት እንቅስቃሴዋችን ማድረግ
– ክብደት መቀነስ 
– ጠቆር ያለ አረንጓዴ ቀለም ያላቸውን በካልስየም የበለጸጉ ቅጠላ ቅጠሎችን፣ ትኩስ ፍራፍሬዎችን፣ ኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ የሚባለው ንጥረ ምግብ የሚገኝባቸውን የቀዝቃዛ አካባቢዎች ዓሣ አዘውትሮ መመገብ
– በፋብሪካዎች በመዘጋጀታቸው ምክንያት የተፈጥሮ ባሕርያቸውን ያጡና የቅባት ክምችት ያላቸውን ምግቦችን አለመመገብ

Advertisement