የሴት ልጅ ግርዛት – Female Circumcision

የሴት ልጅ ግርዛት ነባር ባህላዊ ልምድ ነው። ይህ ሆነ ተብሎ ውጫዊ የሴት ብልት መቁረጥ ወይም መለወጥ ነው። የሴት ልጅ ግርዛት አንዳንድ ጊዜ የሴት ልጅ ብልት መቁረጥ ወይም የሴት ብልት ጉዳት/መተልተል በሚል ይጠራል።

የሴት ልጅ ግርዛት በሴቶችና በልጃገረዶች ላይ ምንም የጤና ጥቅም የለውም እንዲሁም በወሲባዊ ግንኙነትና በስነተዋልዶ ጤና ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።

ሰውነታችንን ለመቆጣጠርና ለመከላከል፤ ሁላችንም በክብር መስተናገደ አለብን። እንደ ሰብአዊ ፍጡር ይህ የእያንዳንዱ መብት ነው።

 

ጤናን በተመለከቱ ጉዳዮች

የሴት ልጅ ግርዛት በጤና ላይ የአጭርና የረጅም ጊዜ ከሚከሰት ችግሮች ከዚህ በታች ያለን ያካትታል:

  • ከባድ ህመም
  • ትኵሳት
  • ጠባሳ መፍጠር
  • የነርቭ መቆጣት/ህመም (በነርቭ ህዋሳት ላይ እብጠት ወይም ቁስል)
  • የፉኛና የሽንት ቁስለት • በሚሸኑበት ጊዜ ህመም
  • በወር አበባ ጊዜ ወይም በወሲባዊ ግንኙነት ጊዜ ህመም
  • በሽንት መተላለፊያ ቧንቧ ላይ ቁስለት
  • በሚሸኑበት ጊዜ ህመም
  • በሚወልዱበት ጊዜ ችግሮች ማለት እንደ ብልት ቀዳዳ ጥበትና ጠባሳ ስላለ የማህጸን መቀደድ ይፈጠራል።
  • ሞት

4 የሴት ልጅ ግርዛት ዓይነቶች

ዓይነት/Type 1 ወይም Sunna ኪንጥርን በከፊል ወይም ሁሉንም ማስወገድ (የሴት ብልትን ትንሽ፣ ስሜታዊ የሆነን ክፍል) ወይም የቂንጥርን ሽፋን (በቂንጥሩ ዙሪያ ያለን ቆዳ)።

ዓይነት/Type 2 ወይም Sounna ኪንጥርንና ትንሹን ከንፈር የመሰለን ብልት በከፊል ወይም ሁሉንም ማስወገድ (በሴት ብልት ውስጥ ያለን ከንፈር መሳይ ሽፋን ቆዳ) ይህም ከትልቁ ከንፈር የመሰለን ብልት (በሴት ብልት የሚሸፍን ትልቅ የታጠፈ ቆዳ) ጋር ወይም ሳይጨምር ማስወገድ።

ዓይነት/Type 3 ወይምመዝጋት/Infibulation (Pharaonic) በእምስ ዙሪያ ያለን ትንሹንና ትልቁን ከንፈር የመሰለ ብልት በከፊል ወይም ሁሉንም ማስወገድና በእምስ ዙሪያ ትንሽ ቀዳዳ ለሽንትና ለወር አበባ መውጫ ብቻ በመተው መለጠፍና ማሸግ።

ዓይነት/Type 3 አሰራር ቂንጢርን በማውጣት ወይም ባለማውጣት ይካሄዳል።

ዓይነት/Type 4 ወይም የሚያካትተው ሁሉንም የሴት ብልት ዙሪያ ይህም ለህክምና ላልሆነ ምክንያት የመንደልን፣ መውጋት፣ ንቅሳት፣ መጫር፣ ብልትን ማራዘምና ማጨማደድን ያካትታል።

 

በዓለም ዙሪያ 200 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶች የሴት ግርዛት እንደተደረገ ነው። ይህ ልምድ በአፍሪካ፤ ማእከላዊ ምሥራቅና በሳውዝ ኣሜሪካ ባሉት ማህበረሰባትና አንዳንድ የጎሳ ቡድኖች ሊገኝ ይችላል ይህም የሚከተሉትን ያካተተ ነው:

  1. በኒን
  2. ቡርኪና ፋሶ
  3. ካመሩን
  4. ሰንትራል አፍሪኻን ሪፑብሊክ
  5. ቻድ ኮሎምቢያ
  6. ኮተ ዲ’ኢቮረ
  7. ኮንጎ ዲሞክራቲክ
  8. ሪፑብሊክ ጅቡቲ
  9. እኳዶር
  10. ግብጽ
  11. ኤርትራ
  12. ኢትዮጵያ
  13. ጋምቢያ
  14. ጋና
  15. ጊኒያ
  16. ጉኒያ-ቢሳው
  17. ህንድ
  18. ኢንዶነሺያ
  19. ኢራን
  20. ኢራክ
  21. ኬኒያ
  22. ላይቨሪያ
  23. ማላያዥያ
  24. ማሊ
  25. ሞሪታኒያ
  26. ናይጀር
  27. ናይጀሪያ
  28. ኦማን
  29. ፓኪስታን
  30. ፐሩ ሰነጋል
  31. ሰራ ሊዮን
  32. ሲንጋቦር
  33. ሶማሊያ
  34. ስሪ ላንካ
  35. ስታት ኦፍ ፓለስቲን እና
  36. እስራኤል
  37. ሱዳን
  38. ታንዛኒያ
  39. ቶጎ
  40. ኡጋንዳ
  41. ዩናይትድ አረብ ኢሚራትስ
  42. የመን
  43. ዛምቢያ

ለሴት ልጅ ግርዛት የተጀመረው እንደማይታወቅና በሃይማኖት ጠቀሜታ አለው። የሴት ልጅ ግርዛት ዓይነቶች በማህበረሰቦችና በጎሳ/ብሄር ቡድኖች መካከል የተለያየ ነው። በዓለም ዙሪያ ያሉት አገሮች የዚህን ዓይነት ድርጊት እንዳገዱትና በህገወጥነት እንዳስቀመጡት ነው። ስላለን ባህላዊ ልምዶች መነጋገርና መወያየት አስፈላጊ ነው። ባህላችንን እንወዳለን፤ ነገር ግን ለሌላው ጉዳት ሊያመጣ የሚችለውን ልምድ ማስወገድ ይኖርብናል።

ምንጭ: ነጥ

 

Advertisement