የራስ ምታትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ልምዶቻችን – Habits Which Could Cause Headache

የራስ ምታት ህመም ሲሰማን ላለፉት ሰዓታት የተጠቀምናቸውና ለህመሙ ሊያጋልጡን ይችላሉ ብለን የምናሰባቸው ነገሮችን ለማስታዎስ መሞከር የተለመደ ነው።

በዚህም ለራስ ምታት የሚዳርጉን ነገሮችም ከቀላል እስከ ውስብስብ ደረጃ ሊደርሱ ይችላሉ።

አንዳንዴም ጉዳዮች እኛ ከምናስበው በላይ ከፍተኛ የህክምና ክትትል የሚጠይቁ ሊሆኑ እንደሚችሉም ነው መረጃዎቹ የሚጠቁሙት፣ ለምሳሌ የአዕምሮ ውስጥ እጢን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።

በሎስ አንጀለስ የስፖርት ኒውሮለጂና የህመም ማስታገሻ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ቨርኖን ዊሊያም እንደተናገሩት፥ የራስ ህመም የሚከሰተው የጭንቅላት የደም ስሮች፣ ጡንቻዎችና ነርቮች ከሚጠበቀው በላይ ሲነቃቁ ወይንም የንጥረ ቅማሞች ለውጥ ሲኖር ነው።

የራስ ምታት ህመም መንስኤዎች የተለያዩ ቢሆንም ሊያባብሷቸው ከሚችሉ ተያያዥ ልምዶች መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ቀርበዋል።

  1. ቀይ ወይን መጠጣት

አልኮል በተለይም ቀይ ወይን መጠጣት ለእራስ ምታት ህምም እንደሚያጋልጥ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሆኖም እንዴት መንስኤ ሆነ በሚለው ላይ ግን መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆነን የምናስቀምጠው የለም ይላሉ።

በሚቺጋን ዩነቨርሲቲ የጡንቻ ነርቭ መድሃኒት ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አሚት ሳችዴቭ አልኮል መጠጣት በደም ዑደት ሂደት ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ ተናግረዋል።

በዚህም የእጅ፣ የእግርና የሌሎች አካሎች የደም ስሮች በመለጠጥ የደም ዑደት ፍጥነት የሚቀነስ ሲሆን፥ ልብ የደም ዑደት እንቅስቃሴውን ለማፍጠን ምቷን የምትጨምር መሆኗን ገልጸዋል።

በአልኮሉ ሳቢያ የሚፈጠረውን የአዲስ ክስተት ስሜት ነርቮቹ ወደ ጭንቅላታችን በመላክ የራስ ምታት ህመም እንዲሰማን የሚያደርጉ መሆኑን በካሊፎርኒያ ሳንታሞኒካ የቅዱስ ዮሃንስ ጤና ማዕከል የነርቭ ዶክተር የሆኑት ዳኔል ፍራንስ ተናግረዋል።

  1. የተቀነባበሩ የስጋ ውጤቶችን መመገብ

የተቀነባበሩ የስጋ ምግቦችን ለረጅም ጊዜ ሳይበላሹ ለማስቀመጥ የሚጨመሩ ቅመሞች ለራስ ምታት መንስኤ ሊሆኑ እንደፈሚችሉ ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።

የተቀነባበሩ የስጋ ምግቦች ለምግብነት ሲያገለግሉ የቆዩ ቢሆንም በቅርብ ጊዜ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በአንዳንድ ሰዎች አፍ ውስጥ ያሉ ባክቴሪዎች በተቀነባበሩ ምግቦች ላይ ከሚገኙ ናይትሬት ከተባሉ ንጥረ ነገሮች ጋር በመዋሀድ የሚፈጥሩት ኬሚካል ለራስ ምታት ህመም ያጋልጣል ተብሏል።

  1. በቂ እንቅልፍ ያለማግኘት

በቂ እንቅልፍ ያለማግኘትና ጭንቅላት ላይ የሚደርስ ውጫዊ ግጭት ለራስ ምታት ህመም መከሰት ሌሎች መንስኤዎች ናቸው ተብሏል።

ሁሌም የተስተካከለ እንቅልፍ ለማግኘት ባይቻልም በተቻለ መጠን ጥሩ እንቅልፍ ለማግኘት የሚያስችሉ አማራጮችን መጠቀም እንደሚያስፈልግ ነው በመረጃው የተጠቀሰው።

ችግሩ ስር የሰደደ ከሆነም የዘርፉ ሀኪሞችን ማማከርም ተገቢ መሆኑ ተመላክቷል።

  1. ምግብን በሰዓቱ አለመመገብ

በተለያዩ የስራና የማህበራዊ ጉዳዮች ጫና ቁርስ፣ ምሳና እራት የምንመገብበት ሰዓታችንን ለማስተካከል እንቸገር ይሆናል።

ነገር ግን የአመጋገብ ስርዓታችን የምናዛባ ከሆነ ለእራስ ምታት አንዱ መንስኤ እንደሚሆን ነው የተገለጸው።

የአመጋገብ ስርዓትን ማዛባት ከረሀብ ሰሜት በተጨማሪ ለሰውነት ድርቀት የሚያጋልጥ ሲሆን፥ የረሀብ ስሜትና ድርቀቱ ደግሞ ለእራስ ምታት ስሜት መንስኤ እንደሆነ ነው በዘገባው የተገለጸው።

  1. ያልተስተካከል የሰውነት አቋም

ከህፃንነታችን ጀመረው እናቶች የሆነን ቀጥ ብለን እንድንሄድ እንድንቀሳቀስና እንድንታይ ጥረት የሚያደርጉ ሲሆን፥ ይህ ልምድ መዳበር እንዳለበት ዶክትር ፍራንስ ይመከራሉ።

በዚህም ቀጥ ያለ የሰውነት አቋም እንዲኖረን ጥረት በማድረግ የራስ ምታት ስሜትን ይቀንሳል ተብሏል።

ምክንያቱም የሰውነታችን አቋም ቀጥ ያለ ካልሆነና የሰውነታችን ሚዛን ወደ ፊታችን ያዘነበለ ከሆነ የአንገታችን ነርቮች ምቾት ስላማይሰማቸው ለሴንትራል ነርብ ስርዓና ለጭንቅላታችን መልእክት በማድረስ የህመም ስሜት እንዲከሰት እንደሚያደረጉ ነው ተመራማሪዎቹ የገለጹት።

  1. ውጥረት

ሰዎች ለውጥረት በሚዳረጉበት ጊዜ ለቀላል፣ መካከለኛና ከፍተኛ የራስ ምታት እንደሚጋለጡ ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.