አይናችን ስለ ጤናችን ምን ይናገራል? – What Do Our Eyes Tell Us About Our Health?

በአይኖቻችን ላይ የሚታዩ ለውጦች የእይታ ችግር፣ የስኳር በሽታ፣ ጭንቀት እና መሰል ችግሮች መጋለጥን ሊያሳዩ ይችላሉ።
በአይናችን የሚታዩ ያልተለመዱ ምልክቶችን ማስተዋል ከቻልን የችግሩን ምንጭ በመረዳት ለመፍትሄው መንቀሳቀስ እንጀምራለን።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በአይናችን ላይ የሚታዩ ምልክቶች ስለሚሉት ነገሮች እንዲቀህ ቀርቧል።

1. የአይን ቆብ እብጠት
በአይን ቆብ ላይ የሚወጣ እብጠት መጠነኛ የህመም እና የማቃጠል ስሜት ሊኖረው ይችላል፤ ብዙ ጊዜ በጥቂት ቀናት ውስጥም ይጠፋል።
ይሁንና እብጠቱ ከአይናችን ቆብ ላይ እስከ ሶስት ወራት ድረስ የማይጠፋ ከሆነ ላልተለመደው “ሳባካሲየስ ግላንድ ካርኪኖማ” ካንሰር መጋለጥን ሊያመላክት ይችላል።
በተመሳሳይ ቦታ ለረጅም ጊዜ በአይን ቆባችን ላይ የሚወጣ እብጠትም ከላይ ለጠቀስነው የካንሰር አይነት ተጋላጭ መሆንን ሊያሳይ እንደሚችል ተገልጿል።

2. የቅንድብ ፀጉር መርገፍ
የቅንድብ ፀጉር በተለያዩ ምክንያቶች ሊረግፍ ይችላል። የቅንድባችን ጫፍ (ሳሳ ያለው ክፍል) ፀጉር መርገፍ ከጉሮሮ ጋር ለተያያዘ ችግር መጋለጣችን ያሳያል።
የአይን ሽፋሽፍት ፀጉር መርገፍ ደግሞ ለካንሰር ከመጋለጥ ጋር ሊያያዝ ይችላል ተብሏል።

3. የአይን መርገብገብ
ጭንቀት ከሚንፀባረቅባቸው መንገዶች አንዱ የአይን መርገብገብ ነው። ብዙ ጊዜ አይናችን የሚርገበገብ ከሆነ ለጭንቀት መጋለጣችን ያመለክታል የሚሉት ዶክተር ሄርዝ፥ በመሆኑም በቂ እረፍት ማግኘት ይሆርብናል ብለዋል።

4. የእይታ ብዥታ – ስኳር
አይናችን በጥራት መመልከት ሲያቅተውና ነገሮችን በብዣታ እንድናይ ሲያስገድደን በአይናችን ላይ የተፈጠረ ችግር መኖሩን መጠራጠር ይኖርብናል።
ብዥ የሚል እይታ ከአይናችን ጋር የተያያዘ ብቻ ሳይሆን እንደ ስኳር ህመም ያሉ በሽታዎች መጋለጥም ሊያመላክት ይችላል።
በነሃሴ 2014 የተደረገ ጥናት 73 በመቶ የስኳር በሽተኞች የእይታ ችግር እንዳለባቸው አረጋግጧል።
የአይን ሀኪሞች ብርሃንን ተቀብሎ ምስልን ወደ አዕምሮ የሚልክ የአይን ክፍልን (ረቲና) በመመልከት ለስኳር በሽታ መጋለጥን ማረጋገጥም ይችላሉ።

5. በአይን ብሌናችን ዙሪያ የሚታይ ነጭ ቀለበት – ኮሌስትሮል
በአይናችን ብሌን ዙሪያ ነጭ ቀለበት መፈጠር ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ቢሆንም ሰውነታችን ከፍተኛ ኮሌስትሮል መጠን መያዙን ሊጠቁም ይችላል።

6. የአይን ድርቀት – አለርጂ
የአይን ድርቀት እና በዙሪያው ያለ ቆዳ መሸብሸብ ብዙ ጊዜ አይናችን ከማሸት የመነጨ ሊሆን እንደሚችል ዶክተር ሀርዝ ይናገራሉ።
በተደጋጋሚ አይናችን ማሸት የቅንድባችን ፀጉር እንዲረግፍ ያደርጋል። ይህም ለአለርጂ ሊያጋልጥ እንደሚችል ነው የገለጹት።

7. የአይን መቅላት
የአይን መቅላት ብዙ ጊዜ ከኢንፌክሽን ጋር አይያያዝም፤ ምናልባትም የከፍተኛ ድካም ምልክት ሊሆን ይችላል።
እንቅልፍ ማጣትም አይናችን እሹኝ እሹኝ እንዲልና እንዲቀላ ሊያደርገው እንደሚችል ዶክተር ሀርዝ ጠቁመዋል።

8. በነጩ የአይናችን ከፍል የሚታዩ ቢጫ መሳይ ምልክቶች
ብዙ ጊዜ ለፀሃይ ብርሃን የሚጋለጡ ሰዎች በነጩ የአይናቸው ክፍል ቢጫ መሳይ ምልክቶች ሲወጡባቸው ይታያል።
እነዚህ ምልክቶች አንዳንድ ጊዜ ለካንሰር መጋለጥን ሊያመላክቱ ይችላሉ ቢባልም፥ ብዙ ጊዜ ከፀሃይ ብርሃን ተጋላጭነት ጋር ይያያዛሉ ብለዋል ዶክተር ሀርዝ።
በ2013 የፀሃይ ብርሃን ጨረሮች በአይን ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለማየት የተደረገው ጥናት የፀሃይ ብርሃን መከላከያ መነፅሮችን የሚያደርጉ ሰዎች አይናቸው ነጩ ክፍል ላይ ቢጫ ምልክቶች አይወጡባቸውም ብሏል።

9. ቢጫ አይን – ጉበት
የአይናችን ነጩ ክፍል ወደ ሙሉ ቢጫነት መቀየር ሰውነታችን የጤና እክል እንደገጠመው በግልፅ ያሳያል።
የአይን ቢጫ መሆን ከቀይ የደም ህዋሳት መፈረካከስ በኋላ የሚፈጠረው ቢሊሩቢን የተሰኘ ቢጫ ውህድ መብዛትን ያመለክታል።
ጉበታችን ህዋሳቱን በደምብ ማጣራት ካልቻለ አይናችን ወደ ቢጫነት ይቀየራል።
ሁኔታው በወጣቶች ላይ በስፋት የማይሰተዋል ሲሆን አንዳንድ ህጻናት ጋር ቢጫ አይን ይዘው ሊወለዱ ይችላሉ።
አብዛኛውን ጊዜ ለዚህ ችግር የሚጋለጡ ሰዎች ከአልኮል ጋር ለተያያዘ የጉበት በሽታ የተጋለጡ ናቸው።

10. የአይን መቅላት እና እምባ ማቀርዘዝ
ለረጅም ጊዜ ኮምፒውተር ላይ አፍጥጦ ማሳለፍ እና በተለያዩ ስራዎች መወጠር አይናችን በእንባ እንዲሞላ ያደርገዋል።
የአይናችን ነጩ ክፍል በተወሰነ መልኩ መቅላትም ከዚሁ ጋር ሊያያዝ ይችላል።
ከዚህ ውጭ ግን በጉንፋን ምክንያት የመጣ ሊሆን ይችላል ።

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

4 Comments

  1. I must show appreciation to the writer just for rescuing me from this type of setting. After surfing around throughout the world wide web and coming across basics which were not powerful, I believed my life was done. Being alive without the presence of solutions to the difficulties you have sorted out by means of your good article content is a serious case, and the ones that would have negatively affected my entire career if I had not encountered your web page. Your good expertise and kindness in handling all areas was very helpful. I don’t know what I would’ve done if I had not discovered such a stuff like this. I’m able to now look forward to my future. Thanks for your time very much for your professional and sensible guide. I won’t think twice to recommend your site to any individual who ought to have direction on this matter.

Comments are closed.