የመንታ እርግዝና

ተጨማሪ ወጭ ሳያወጡ የትኞቹንም ችግሮች በቀላሉ በቤትዎ ከህክምና ባለሙያ ጋር በስልክ በማወያት ያለብዎ የጤና ችግር ተባብሶ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት ወደ ዶክተር አለ! 8809 ጤናን በቤትዎ የማማከር አገልግሎት የጥሪ ማዕከል በመደወል ጤናዎንና ወጭዎን ይጠብቁ፡፡

አንዲት ሴት መንታ ስታረግዝ ምን ማወቅ አለባት?
በእርግዝና ወቅት የሚታዩት አብዛኞቹ ለውጦች በመንታ እርግዝና ላይ ይጋነናሉ።
ለምሳሌ፦ ድካም፣ የወገብ ህመም፣ የእግር ማበጥ፣ ክብደት መጨመር… ወዘተ።

መንታ ጽንስ ያረገዘች እናት ለአንድ ጽንስ ከምትመገበው የእለት የምግብ መጠን በላይ እንድትመገብ ይመከራል። ይህም ነፍሰ ጡር ከመሆንዋ በፊት ከምትወስደው መጠን በተጨማሪ 600 ኪሎ ካሎሪ መውሰድ ይጠበቅባታል።
ከዚህ በተጨማሪ መንታ ያረገዘች እናት ማወቅ ያለባት በእርግዝና ጊዜ ለጤና ችግሮች የመጋለጥ እድሏ ከፍተኛ ስለሆነ ተገቢውን ክትትልና የህክምና እርዳታ
ማግኘት አለባት።

ሊያጋጥሙ የሚችሉት ችግሮች ዋና ዋናዎቹ፤
· የደም ማነስ
· የጽንስ አቀማመጥ መዛባት
· የደም ግፊት
· የስኳር ህመም
· በማህጸን ደም መድማት
· የምጥ ያለግዜው መምጣት
· ከወሊድ በኋላ ከፈተኛ ደም መፍሰስ የመሳሰሉት ናቸው።

ስለሆነም አንዲት መንታ ያረገዘች ሴት በእርግዝናዋ ወቅት ጥብቅ የሆነ የእርግዝና ክትትል ሊኖራት ይገባል!!!

ውድ የዶክተር አለ ተከታታይ በዚህ ፔጅ ጠቃሚ መረጃዎችን እናቀርባለን ፤ እንወያያለን እንዲሁም ለሚነሱ ጥቅዎች ሞያዊ ምላሽ እንሰጣለን ፡፡ ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 2 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ 8809 ቢደዉሉ የዶክተር አለ! ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.