የ14 አመቷ ታዳጊ አበራሽ በቀለ ጠልፎ አስገድዶ የደፈራትን ግለሰብ መግደሏ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ ነበር። አበራሽ በግድያ ክስ ተመስርቶባት ማረሚያ ቤት የነበረች ሲሆን የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ጥብቅና ቆመውላት ነፃ ሆናለች።

ይህንን እውነተኛ ታሪክም ዕውቅና በመስጠት ከጥቂት አመታት በፊት ዘረሰናይ ብርሃኔ መሐሪ ወደ ፊልም በመቀየር አዘጋጅቶታል። ፊልሙ ታዋቂዋን የሆሊውድ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊን በኤክስኪውቲቭ ፕሮዲውሰርነት ከማሳተፉ በተጨማሪ ሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫልን ጨምሮ ብዙ ሽልማቶችን ማግኘት ችሏል።

ከዚህ ፊልም ስኬት ጀርባ ያለው ዘረሰናይ በአሁኑ ወቅት በትልቅ በጀት ‘ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊ’ የሚል ፊልም እየሰራ ነው። በዚህ ፊልም ላይ ታዋቂዋ ዳኮታ ፋኒንግን ጨምሮ የአኳ ማን ተዋናዩ ያያ አብዱል ማቲን፣ የቢግ ባንጉ ኩናል ናይር የተሳተፉበት ሲሆን ከኢትዮጵያም ታዋቂዋ ሙዚቀኛ ዘሪቱ ከበደ ተሳትፋበታለች።

ከዩኒቨርስቲ ኦ ኦፍ ሳውዘርን ካሊሮርኒያ በፊልም የተመረቀው ዘረሰናይ ብርሃነ በአዲሱ ፊልሙና በሙያው ዙሪያ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ቢቢሲ፦ ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊ የተሰኘው ፊልም ቀረፃው ተጠናቋል ?

ዘረሰናይ መኃሪ፦ ቀረፃው ተጠናቋል። ወደ አራት ሳምንት የሚሆን አየርላንድ የቀረፅን ሲሆን በመቀጠልም ድሬዳዋና ሐረር ከተሞች ለ17 ቀናት ያህል ቆይተን ቀረፃውን አጠናቀናል። በዚህ አይነት ደረጃ ፊልም ሲሰራ ሂደቱ በጣም የተለየ ነው። ለሂደቱ አዲስ ባልሆንም በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረን ቀረፃ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የፊልም ባለሙያዎችን ከሆሊውድ ተዋናዮች ጋር ለማዋሃድ መስራት ነበረብን። ብዙ ፈታኝ ጉዳዮች ቢያጋጥሙንም ካሰብነው በላይ በሚያኮራ መንገድ ነው የጨረስነው።

ቢቢሲ፦ በጣም ትልቅ በጀት ያለው እንደመሆኑ መጠን ኢትዮጵያ ውስጥ መቅረፅ ፈታኝና በጎ ነገሮቹ ምን ነበሩ?

ዘረሰናይ፦ ጥሩነቱ ኢትዮጵያ ውስጥ መቅረፅ መቻላችን በምስል ደረጃ ብዙ አስደማሚ ነገሮችን ሰጥቶናል። በሚገርም ሁኔታ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ሞሮኮን አስመስለን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የቀረፅነው። ያለን የመልክአ ምድር ብዛትና አይነት የትኛውንም አገር ማስመሰል ይቻላል። ነገር ግን ሌሎች ሃገሮች ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ ብንቀርፀው ደግሞ ጥቅማጥቅሞች ይኖሩት ነበር።

ፊልሞች ወደየሃገሮቻቸው እንዲመጡና መዋዕለ ንዋያቸውን በሀገሮቻቸው ላይ እንዲያፈሱ የዘረጉት ስርአት አለ። ከግብር እፎይታ ጀምሮ የፊልም ቁሳቁሶች በነፃ ነው የሚገቡት፤ የሰለጠነ የሰው ኃይል አለ፤ የፊልም እቃዎቹ እንደልብ ነው። ሆኖም ግን የፊልሙ ታሪኩ ሐረርና ድሬዳዋ ስለሆነ የሚያጠነጥነው፤ ቦታዎቹ ያላቸውን ታሪካዊ ምስል በሌላ ቦታ መተካት አይችልም።

ኢትዮጵያ ውስጥ መምጣታችን በገንዘብ ደረጃ ጎድቶናል፤ ዕቃው በሙሉ ከአየርላንድ ተጭኖ ነው የመጣው። ከዚህም በተጨማሪ ሰላሳ ስድስት የፊልም ባለሙያዎች አስመጥተናል። ያ ሁሉ ጉድለት እያለ በምስል ደረጃ የሚሰጠንን ነገር መተካት አንችልም። በሱ በጣም ደስተኛ ነኝ።

ከዚህ ሁሉ በላይ ትልቁ ችግራችን የነበረው የፊልም ገንዘብ (ፊልም ፋይናንሲንግ)ና የሶስተኛ ሀገር ስምምነት ( ሰርድ ካንትሪ ትሪቲ ) የለም። ለምሳሌ ሁለቱ ሃገራት አየርላንድና ካናዳ በመካከላቸው ስምምነት ስላላቸው መንግሥት በጥበብ (አርት ኢንዳውመንት) በኩል ድጋፍ አድርጎላቸዋል።

ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር እንዲህ አይነት ስምምነት ያስፈልጋታል። ያ ደግሞ ለኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች ብዙ በር ሊከፍትልን ይችላል። ምክንያቱም እንደሚታወቀው ለፊልም የተመደበ ገንዘብ (ፊልም ፋይናንሲንግ) የለም። ማንም ሰው በራሱ ያለውን መኪና ሸጦ፣ ወይም ደግሞ ቤቱን አስይዞ ነው ፊልም የሚሰራው። እንደዛም ሆኖ የሚሰሩት ፊልሞች ከአገር ውጭ መታየት ባይችሉም ሀገር ውስጥ በሚታዩበት ወቅት ትርፉ ይህ ነው ባይባልም ገንዘብ ያስገኛሉ።

ድጎማ ቢኖር፣ ለማስታወቂያ ገንዘብ ቢኖር፤ ታሪኩ ሲፃፍ ጀምሮ ፊልሙን ለማዳበር የሚደግፍ ቢኖር የሰውም የማየት ፍላጎት ሆነ ለፊልም ባለሙያዎች የሚከፈለው ገንዘብ የላቀ ይሆናል። ሌላ ስራ እንዳይሰሩና በዚህ በያዙት ሙያ ቀጥለው ሙያቸውን እንዲያዳብሩ ማድረግ ይቻላል። ምንም እንኳን የተለያዩ የሚኒስትር ቢሮዎች ድጋፍ አድርገውልን ቀለል ቢልልንም፤ የፊልም እቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት በጣም ከባድ ነበር።

ቢቢሲ ፦ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊን‘ ወደ ማዘጋጀቱ ስራ እንዴት ገባህ? ለፊልም እንዲመች አድርገህፃፍከው አንተ ነህ ወይስ የመፅሀፏ ደራሲ ለዳይሬክተርነቱ ሚና መረጠችህ? ሂደቱን አጫውተን

ዘረሰናይ፦ ታሪኩን ያነበብኩት ከአራት አመት በፊት በርሊን የመጀመሪያ ፊልሜን ድፍረትን ልናሳይ በርሊን ሄደን እያለ ነው። መፅሀፉ የተፃፈው በካሚላ ጊብ ሲሆን፤ ሁለት ካናዳውያን ፕሮዲውሰሮች ከደራሲዋ ጋር ተስማምተው ለፊልም እንዲመች አድርገው ፃፉት። በዛን ጊዜ አዘጋጅ እየፈለጉ በነበረበት ወቅት በአጋጣሚ ድፍረትን መመልከታቸውና ድፍረትም የተመልካች ሽልማት ማሸነፉ፤ ከዚያም በፊት ሰንዳንስ ላይም አሸንፎ መምጣቱን በማየት እንዳዘጋጅ ጠየቁኝ። ፅሁፉን ለማንበብ ሁለት ሰዓትም አልፈጀብኝም ፤ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠሁ በመሀል ነው ያነበብኩት፤ እዛው ነው በፍጥነት ነው ፊልሙን ለመስራት የወሰንኩት። ታሪኩን እኔ አልፃፍኩትም። መፅሀፉ ላይ ከነበረው ወደ እይታ እንዴት ይመጣል በሚለው መንገድ አንዳንድ ጉዳዮችን የአርትኦ ስራ (ኤዲት) ሰርቻለሁ።

ቢቢሲ፦ ስለ ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊ ትንሽ ንገረን? ለምን ፊልሙን መረጥከው?

ዘረሰናይ፦ ልብወለድ ታሪክ ነው። ነገር ግን ታሪኩን የሰማው ሰው በሙሉ እውነተኛ ታሪክ ነው ብሎ ነው የሚያስበው። ታሪኩ የ1966 አብዮትን ለሚያውቅና ለኔና ከኔም ከፍ ላሉት የቅርብ ታሪክ ነው።መቼቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረገ ፊልም ነው። በዛን ጊዜ እምነቷን ወደ እስልምና የቀየረች አንዲት የሃያ አመት እንግሊዛዊት ከሞሮኮ የቢላል አልሀበሺን የትውልድ ቦታ ለማየት ወደ ኢትዮጵያ ትመጣለች። በኢትዮጵያ ቆይታዋም ኢትዮጵያውያኖች መኖሪያ ሰጥተዋት፤ እየኖረች እያለ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ዶክተር ጋር ግንኙነት ትመሰርታለች። በመሀል ለውጡ ተከሰተ፤ እሷ ደግሞ ብትወለድበትም ወደማታቀው ወደ እንግሊዝ አገር ትመለሳለች። ታሪኩ የሚያጠነጥነው ኢትዮጵያ እንዲሁም ሞሮኮ ውስጥ የነበራትን ቆይታ እንዲሁም እንግሊዝ አገር በስደት ከሄደች በኋላ የነበራትን ህይወት ነው። ዋናዋ ገፀ ባህርይ እራሷን እንደ ኢትዮጵያዊ አድርጋ የምትቆጥር ሲሆን እንግሊዝም ከሄደች በኋላ ከኢትጵያውያን ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራት።

ቢቢሲ፦ የአብዮቱን ጊዜ ማወቅህና ኢትዮጵያዊ መሆንህ ፊልሙን በተሻለ መንገድ እንድነግር ረድቶኛል ብለህ ታስባለህ?

ዘረሰናይ፦ በጣም፤ ፀሀፊዋ ነጭ ነች። የባህል አንትሮፖሎጂ ተማሪ እያለች ኢትዮጵያ ውስጥ በሰባዎቹ መጥታ ስለ ሀረር ሴቶች ፅፋለች። ወደ ኃገሯም ከተመለሰች በኋላ ይህንን መፅሀፍ ፃፈች። የዛን ጊዜ የነበረውን ታሪክ ማወቄና መስማቴ፤ በተለይም ኢህአፓና መኤሶን ውስጥ የነበሩ ግለሰቦችን ታሪክ ማወቄ ለኔ ፊልሙን እንዳዳብረው በትልቅ ደረጃ ረድቶኛል። ምክንያቱም ፊልሙ ላይ በተለይ ኢትዮጵያዊው ገፀ ባህርይ ዶ/ር አዚዝ ከዶክተርነቱና ከፈረንጇ ጋር ካላት ግንኙነት ውጭ ስለሱ ማንነት የሚታወቅ አልነበረም።

ምን ያህል ለአገሩ፣ ለነበረው ለውጥ እንደሚቆረቆር እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች መፅሀፉ ላይ የጎሉ አልነበሩም። ከማቃቸው ታሪኮች፣ ካነበብኳቸው መፃህፍት ወስጀ ገፀባህርዩን በደንብ አዳበርኩት። በዛን ጊዜ የነበሩ ወጣቶች እኛ ያልነበረንን አይነት ኃይል ነበራቸው። ያገሪቷን ፖለቲካዊ መንገድ መቀየርና ማሽከርከር የቻሉ ወጣቶች ነበሩን። እናም እሱ ነገር ተድበስብሶ እንዲያልፍ አልፈለግኩም። የኢትዮጵያን ቦታ በታሪክ ላይ ማወቅ፤ ባህላችንን፤ ታሪኩን ከማያውቅ ሰው በበለጠ ፊልሙን እንድሰራ ረድቶኛል። ይሄ እንግዲህ ፊልሙ ሲወጣ የምናየው ይሆናል።

ቢቢሲ፦ ምዕራባውያን ወይም ነጭ የፊልም ጸሀፊዎችና አዘጋጆች ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካን ታሪክ የሚያዩት በራሳቸው መነጽር (ዋይት ጌዝ) ነው ተብለው ይተቻሉ። የአፍሪካውያን ታሪክ በነጮች ሲፃፍ ወይም ሲዘጋጅ ባህሉን ካለማወቅ በደንብ መንገር አይችሉም ይባላል። ስለዚህ ምን ታስባለህ?

ዘረሰናይ፦ አብዛኛውን ጊዜ እውነት ነው። አውሮፓውያን ወይም ነጭ አዘጋጆች የአፍሪካን ታሪክ ሲናገሩ ከራሳቸው እይታ ነው። ይሄ ችግር ያመጣል። በተለይ “ድፍረት”ን ከሰራሁ በኋላ አንድ ዓመት ያህል በየፌስቲቫሉ እየሄድን ፊልሙን ስናሳይ ብዙ ጊዜ ተናግሬዋለሁ። አፍሪካውያኖች የራሳችንን ታሪክ መናገር መቻል አለብን። የአፍሪካዊን ታሪክ የራሳችን ታሪክ የማድረግ ግዴታም አለብን። በሌላ በኩል ነጮቹ ለምን እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ የሚገቡት ስንል ከኋላቸው ይህንን የሚያደርጉ በጣም ብዙ ትልቅ ሀይሎች አሉ።

አንድ ነጭ አዘጋጅ አፍሪካዊ ፊልም መሥራት የሚፈልግ ከሆነ ፊልሙ ፊልም የሚያስብለው በመጨረሻ ወጥቶ ለሕዝብ ሲታይ ነው። ሰው እይታ ጋር ለመቅረብ በጣም ብዙ ገንዘብ ይፈጃል። አንድ ፊልምን ለመስራት ከሚያበቁት ነገሮች መካከል ትልቁ ነገር ፊልሙ የሚሰራጭበት መንገድ ነው። እነዚህ ነገሮች መጀመሪያ ካልተስተካከሉ ፊልሙ ስኬታማ ሆኖ አይወጣም። ስለዚህ አሰራጮች (ዲስትሪቢውተርስ) ኃይል ስላላቸውና አስቀድመው ገንዘብ መስጠት ስለሚችሉ የፊልም ሰሪውን አካሄድ መቀየር ይችላሉ።

ማየትና መሸጥ የሚፈልጉት ፊልሙን ሊያይ ይችላል ብለው የሚገምቱት ዓለም ላይ ያለውን ነጭ ተመልካች ስለሆነ፤ ነጮች በሚያዩትና በሚገባቸው መንገድ ነው ፊልሙን መሥራት የሚፈልጉት።

ለምሳሌ የማልረሳውና ያስደነገጠኝ ትልቅ ነገር አለ። “ድፍረት” ሰን ዳንስ እንዳሸነፈ ስርጭት እየተስማማን እያለ አንድ ጣልያናዊት አሰራጭ በጣም ፊልሙን ወደደችውና ተደራደረች። ፊልሙን በዓለም ለማሳየትም የ “ወርልድ ዋይድ ራይትስ’ መብቱንም መውሰድ ፈለገች። ድርጅቷ ያለው ጣልያን ቢሆንም ጣልያን ሀገር ማሳየት አልፈለገችም። ለምን? ስላት፣ ፊልሙ ውስጥ ምንም ነጭ ገፀባህርይ ስለሌለ ፊልሙን ጣልያን ሀገር ለማሳየትና ለመሸጥ በጣም ይከብዳል አለች።

ያላቸው አስተሳሰብ ወይም አንድን ነገር ለመገንዘብ እነሱን የሚመስል ሰው እዛ ውስጥ መኖር አለበት የሚለው ነገር ነው። በጣም አስደነገጠኝ። ከዛ በተጨማሪ ጃፓን ሀገር “ድፍረት” በየቴአትር ቤቱ ለማሳየት የስርጭቱን መብት ከወሰዱ በኋላ ፖስተሩን መቀየር ፈለጉ። ፖስተሩ ላይ የ13 ዓመት ኢትዮጵያዊት ታዳጊ ነው ያለችው። ተመልካች እሱን ካየ አያይልንም ብለው የአንጀሊና ጆሊን ፎቶ እናድርግበት ወይ? ብለው ጠይቀውናል።

ለተግባራቸው ምክንያት እየሰጠሁ አይደለም ነገር ግን ሌላ ግፊት ሳይኖርባቸው አፍሪካን በአንድ መነጽር ብቻ የሚያዩ ሌሎችም አዘጋጆች አሉ። ለምሳሌ የኢትዮጵያን ባህልና የናይጄሪያን ባህል አንደ አይነት አድርገው፣ አጣምረው ማሳየት የሚፈልጉ አዘጋጆችም አሉ።

የስርጭት መንገዱ እስካሁን በብዛት የተያዘው በነጮችና ለነጮች የሚቀርብ ስለሆነ፤ አንደኛ አፍሪካን እንደ ገበያ አይዩንም። ስለዚህ የነጭ ፊልም ባለሙያዎች ፊልም ሲሰሩ አፍሪካን ለሌላው ሕዝብ እንዴት አድርገው እንደሚያሳዩ ነው። ለዛም ነው እንደዚህ አይነት ፊልሞች ሲሠሩ ታሪኩን በትክክል የመንገር ታሪኩን በደንብ አድርጎ የመወከል ኃላፊነት ያለብን። በዛም ላይ ደግሞ የፈጠራ ችሎታችንን፣ ታሪክ መንገር የምንችል ሰዎች መሆናችንን፣ከሌላው ሀገር ያላነሰ መሆኑን ማሳየትም አብሮ ይመጣል።

ቢቢሲ፦ የአፍሪካ ፊልም ቢሆኑም ብዙ ጊዜ በነጮች የተሞሉ ወይም ዋናው ነጭ ተዋናይ እንደ ጀግና ተስሎ ጥቁር ህዝቦችን የሚታደግ ፊልሞች ለረጅም ጊዜ እናይ ነበር። በባለፉት ጥቂት ዓመታት ግን እንደ ብላክ ፓንተር በጥቁር ተዋንያን የተሞላ ፊልሞችም መታየት ችለዋል። ኔትፍሊክስ ከደቡብ አፍሪካ ፊልም መውሰዱ እና ሌሎች አፍሪካዊ ፊልሞችን ለመውሰድ ክፍት ማድረጉም የተወሰነ እንደተከፈተ የሚያሳይ ይመስላል። “ድፍረት” የነበረውን ዓለም አቀፍ እይታን በማየት፣ አሁንስ ለኢትዮጵያዊ አዘጋጆች ምን ያህል ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ክፍት ነው ብለህ ታስባለህ?

ዘረሰናይ፦ በጣም ውስን ነው። ያም የሆነበት ምክንያት አፍሪካ ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በኢንቨስትመንት ወደ ፊልም ማምጣት የሚችሉ በጣም የተወሰኑ ሀገሮች ብቻ ናቸው። አንደኛ ሥራችን እስካልታየ ድረስ ማንነታችን አይታወቅም። በኔ ላይ የደረሰው ትልቅ ምሳሌ ነው። “ድፍረት”ን ሰራሁ፤ ፊልሙ እድል አግኝቶ ከዓለም ሁለተኛ ትልቅ የሚባል ፌስቲቫል ላይ መሳተፍ ቻለ እናም እዛም ማሸነፍ በመቻሉ የፕሮዲውሰሮችና የአዘጋጆች ቀልብ ያዘ።

ይህንን ስል በኢትዮጵያዊነቴ ወይም በጥቁርነቴ አዝነውልኝ ያደረጉት አይደለም። በስተመጨረሻ ለማናቸውም ቢሆን ቢዝነስ ነው። ባህላችንን ወይም ታሪካችንን መንገር እንዳለ ሆኖ በሌላ መንገድ ደግሞ ስኬታማ ነገሮች ማድረግ መቻል አለብን። ለምሳሌ “ብላክ ፓንተር”ን የፃፈውንና ያዘጋጀውን ራየን ኩግለርን እንውሰድ እኔና እሱ አንድ ትምህርት ቤት ነው የተማርነው። “ብላክ ፓንተር” ሦስተኛ ፊልሙ ሲሆን ከዛ በፊት “ፍሩት ቬል ስቴሽን ” እና “ክሪድ” የተሰኙ በትንሽ በጀት ፊልሞች ሰርቷል።

ይህ እድል ሲሰጠው ደግሞ ከዛ በፊት በነበሩት ፊልሞቹ አብዛኛው ጥቁር ተዋናዮችን አሳትፎ ስኬታማ ስለሆነ ነው። 99% ጥቁር ተዋናዮች ያሉበት አሜሪካዊ ፊልም ፊልም ተሰርቶ ሲወጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የፊልም የደረጃ ሰንጠረዥ በመቆጣጠር ገንዘብም ማግኘት እንደሚችል አሳየ። የኔትፍሊክስም አፍሪካ መምጣትና ከደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያ ፊልም መውሰዳቸው የሚያሳየን ለኛ አዝነውልን ወይም ደግሞ የአፍሪካ ታሪክ እንዲህ ነው ብለው የሚመጡበት ሳይሆን ሁሉም ነገር ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነው።

የአፍሪካ ህዝብ እንደ ትልቅ ገበያ መታየት ጀምሯል። ፊልሞችን ማየት ብቻ ሳይሆን የራሳችንንም ታሪኮች ወደ ውጭ ማውጣት የሚችል ተቋማት መፍጠር እንችላለን። የኢትዮጵያን ፊልሞችን ብናይ በኃይሌ ገሪማ በኩል ስማችን ሲጠራ ቆይቷል። ከዚያም በኋላ ድፍረት፣ ላምብ፣ አትሌቱ በሄዱበት ቦታ አሸናፊ መሆናቸውና ለስርጭት መብቃታቸው በር ከፋች ሆኗል። ከማንኛውም አለም የበለጠ ታሪክ አለን ነገር ግን እሱን መቀየር ካልቻልን የሌሎችን ስራ ተመልካች ወይም የኛን ታሪክ በሌላ እንዲሰራ መፍቀድ ነው።

ቢቢሲ፦ በግልህ ፊልም እንደሚሰራ ሰው ፈተናዎቹ ምንድን ናቸው?

ዘረሰናይ፦ በጣም መአት ችግሮች ናቸው (ሳቅ) ። ከየት ልጀምር መኖሪያየን ኢትዮጵያ ካደረግኩ ሶስት አመት ሆኖኛል። አሜሪካም እያለሁ ለፊልም ገንዘብ ማግኘት ችግር ነው። ለፊልም ገንዘብ የሚሰጡ ብዙ ተቋማት አሉ። ፊልም ላብራቶሪዎችና ፊልም ፌስቲቫሎች አሉ። ነገር ግን ውድድሩ በጣም ፈታኝ ነው።

ከአምስት ሺ ያላነሱ ፎርሞች ይሞላል፣ የፀሀፊው ማንነት፣ ዳይሬክተር ታይቶ አስርና ሃያ ለሚሆኑት ብቻ ተጣርቶ ድጋፍ ይሰጣል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ መስራት ከዚህ የከበደ ነው። ድፍረትን ለመስራት ስምንት አመት ወስዶብናል። አንደኛ አፍሪካዊ (ኢትዮጵያዊ) ታሪክ መሆኑ ብዙ ሰው ሊቀበለው አልፈለገም። ሁለቱ መሪ ተዋንያን ሴቶች መሆናቸውን ደግሞ ሌላው ፈታኝ ጉዳይ ነበር። እኔ ታሪኩን ብቻ ነው ያየሁት የጄንደር (የሥርአተ ፆታው) ፖለቲካው አልገባኝም ነበር።

እድለኛ ነኝ የምለው ፕሮዲውሰሯን ምህረት ማንደፍሮን ማግኘቴ ነው። ዋናውን መንገድ ትተን ፊልሙን መደገፍ የሚችሉ ሰዎች ስናፈላልግ የመጀመሪያውን ድጋፍ ያገኘነው ከታዋቂዋ ሰዓሊ ከጁሊ ምህረቱ ነው። አንድ ስዕሏን ሸጣ ድጋፍ አደረገችልን። ምንም እንኳን ጥሩ ታሪክ እስካለው ድረስ ድጋፍ የሚያደርጉ አይታጡም የሚል እሳቤ ቢኖርም እውነታው ግን ታሪክን እንደ ገንዘብ ዕድል አይቶ ድጋፍ የሚያደርግ አለመኖሩ ነው።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

14 Comments

  1. Your outlook on life is amazing. When it건마 to cooking, no one’s meals are quite as delicious. You are more fun than anyone or anything I know, including bubble wrap.?

  2. Nice post. I be taught one thing more challenging on totally different blogs everyday. It will at all times be stimulating to read content material from different writers and practice a little something from their store. I抎 favor to use some with the content on my weblog whether or not you don抰 mind. Natually I抣l provide you with a hyperlink on your internet blog. Thanks for sharing.

  3. I am usually to blogging and i really admire your content. The article has actually peaks my interest. I’m going to bookmark your website and keep checking for brand new information.

  4. Spot on with this write-up, I truly assume this web site needs far more consideration. I抣l in all probability be again to read far more, thanks for that info.

  5. Youre so cool! I dont suppose Ive learn anything like this before. So good to seek out any person with some unique ideas on this subject. realy thanks for beginning this up. this web site is something that’s wanted on the internet, someone with just a little originality. helpful job for bringing something new to the web!

  6. Youre so cool! I dont suppose Ive read something like this before. So good to search out someone with some unique thoughts on this subject. realy thanks for beginning this up. this web site is one thing that’s wanted on the net, somebody with a bit originality. useful job for bringing something new to the web!

  7. After I originally commented I clicked the -Notify me when new feedback are added- checkbox and now each time a comment is added I get 4 emails with the same comment. Is there any way you may take away me from that service? Thanks!

  8. The subsequent time I learn a weblog, I hope that it doesnt disappoint me as much as this one. I imply, I do know it was my option to read, but I really thought youd have something attention-grabbing to say. All I hear is a bunch of whining about one thing that you may repair in case you werent too busy searching for attention.

  9. I抦 impressed, I need to say. Actually rarely do I encounter a blog that抯 both educative and entertaining, and let me inform you, you’ve gotten hit the nail on the head. Your thought is excellent; the issue is one thing that not sufficient people are speaking intelligently about. I am very completely happy that I stumbled across this in my seek for something regarding this.

Comments are closed.