ያልተፈለገ የሰውነት ክብደት እንዴት ለካንሰር በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል?

ያልተፈለገ የሰውነት ክበደት ለካንሰር በሽታ ሊጋገልጥ በሚችልበት ሁኔታዎች ላይ ተመራማሪዎች አዲስ ጥናት ይፋ አድርገዋል።

በብሪታኒያ የትሪኒቲ ኮሌጅ ተመራማሪዎች ባልተፈለገ የሰውነት ክብደት እና በካንሰር በሽታ መካከል ባለው ተዛምዶ ላይ ባዳረጉት ጥናት መሰረት በየዓመቱ ከሚመዘገቡ 22ሺህ 800 ያህል የካንሰር ህሙማን መካከል ከ20ዎቹ አንዱ በሽታው ካልተፈለገ የሰውነት ክብደት ጋር ተያያዥነት ያለው መሆኑ ተገልጿል።

የሰውነት ክብደት እና የስብ ክምችት እየጨመረ ሲሄድ ሰውነት በተፈጥሯዊ መንገድ ለካንሰር የሚያጋልጡ ‘‘ቲሹዎችን’’ ለማስወገድ የሚገለገልባቸው ህዋሶች በስብ እንደሚሸፈኑ እና ስራቸውን የሚያቋርጡ መሆኑም ተገልጿል።

በዚህም የሰውነት የካንሰር መካላከል አቅም የሚዳከም እና የካንሳር በሽታ ተጋላጭነት ሊጨምር እንደሚችል ተነገሯል።

ካልተፈለገ የሰውነት ክበደት ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የሰውነት የካንሰር በሽታን የመከላከል አቅም እንደገና ለመመለስ የሚያስችል መድሃኒት የማግኘት ተስፋ ያላቸው ተመራማሪዎቹ በዘርፉ ላይ ሰፊ የቤተ ሙከራ ምርምር ላይ መሆናቸውም ታውቋል።

ቀደም ባሉት ጊዚያት ያልተፈለገ የሰውነት ከብደት ለ13 የተለያዩ የካንሰር በሽታ አይነተቶች እንደሚያጋልጥ የሚታወቅ ቢሆንም፥ በሽታው ካልተፈለገ ሰውነት ክብደት ጋር ያለው ግንኙነት ላይ ጥልቅ ጥናት ያልተደረገ መሆኑን በብሪታኒያ ቢትሰን የካንሰር ጥናት ኢኒስቲትዩት ዶክተር ሊዮ ካርሊን ተናግረዋል።

ጥናቱ የምግብ ውህደት ላይ ሰፊ ምርምሮችን በማድረግ በተፈጥሯዊ መንገድ የሰውነት የካንሰር በሽታ የመከላከል አቅም ለማዳበር ሌሎች ጥናቶችን ለማድረግ የሚጋብዝ መሆኑም ነው የተገለጸው።

የሰውነት ክብደትን መቀነስ ከካንሰር በሽታ እራስን ለመከላከል የሚያስችል ቀላል እና ወጭ የማይጠይቅ መሆኑንም ዘገባው ያስረዳል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.