ዋሌት በኋላ ኪስ ማስቀመጥ የሚያስከትለው ጉዳት

ብዙ ወንዶች ዋሌት(የኪስ ቦርሳ) በኋላ ኪሳችን ማኖር እናዘወትራለን።

እንደ ሴቶች ቦርሳ ስለማንይዝም መታወቂያችንን እና ፎቶግራፎችን ጨምሮ ሌሎች ለዘወትር አገልግሎት አስፈላጊ የሆኑና ያልሆኑ ነገሮችን በዋሌታችን እንይዛለን።

ይሄው የዋሌታችን መጠን በተለቀ ቁጥርም ስንቀመጥም ሆነ መኪና ስናሽከረክር የአከርካሪ አጥንታችን ከተፈጥሯዊዉ ሁኔታ በተለየ መልኩ የመዛነፍ ሁኔታ ያሳያል፡፡

የደም ዝውውራችንም በተወሰነ መልኩ እንዲስተጓጎል ያደርጋል።

በዚህም ምክንያት ለወገብ ህመምና እንደ ዲስክ መንሸራተት ለመሳሰሉ ህመሞች እንጋለጣለን።

ባለሙያዎች እንደሚሉት ዋሌት በኋላ ኪስ ማስቀመጥና በአንድ እግራችን ትልቅ ሂል ጫማ መጫማትና በሌላው ስስ ሶል ያለው ጫማ ማድረግ አንድ ናቸው።

በተመሳሳይ ሴቶችም ከባድ ቦርሳ አዘውትረው በአንድ በኩል የሚይዙ ከሆነ የጀርባ አጥንታቸው እንዲዛባና ያልተስተካከለ አቋም እንዲኖራቸው ያደርጋል።

ባለሙያዎቹ ለወንዶቹ እንደ መፍትሄ ያስቀመጡት የዋሌታችንን የውፍረት መጠን በተቻለ መጠን ስስ በማድረግ ሳንሰላች በፊት ኪስ መያዝ መልመድን ነው።

የዋሌት ቦርሳችንን በአሰስ ገሰሱ ከመሙላት ይልቅ እጅግ በጣም የሚያስፈልጉንን ብቻ መያዝም ለዚህ ይረዳናል።

ሴቶችም ልክ እንደ ወንዶቹ ባይሆንም በቦርሳችን በጣም ከባድ ነገሮችን ከመያዝ መቆጠብና በሁለቱም ጎናችን እያፈራረቅን መያዝ ተገቢ ነው ተብሏል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.