አዕምሯችን የሚያዛቡ መጥፎ ልማዶች

  1. እጾች

ለመዝናናት ወይም ከመጥፎ ስሜት ለመውጣትና ነቃ ለማለት ተብለው የሚወሰዱ እጾች አዕምሯቸውን ለማቃወስ ማንም አይደርስባቸውም። እጾች እንደ ሄሮይን፣ ሜታመፌቴሚን እና ኮኬይን የመሰሉ ኬሚካሌችን በመያዛቸው ያለ እድሜያችንን እንድናረጅ በማድረግ ህይወታችን የማሳጠር አቅማቸው ትልቅ ነው። እጾች በሽታ የመከላከል አቅማችንን በመቀነስ ለተለያዩ ኢንፌክሽኖችም ይዳርጉናል። እንቅልፍ ማጣት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት እና ድብርትም እጾችን ከመውሰድ የሚመጡ ችግሮች ናቸው።

2. አልኮል

አልኮል ከልክ በላይ በምንወስድበት ስአት የምግብ አምሮታችንም በዚያው ልክ እንደሚቀንስ ነው የሚነገረው። ከአልኮል የምናገኘው ካሎሪ የረሃብ ስሜታችንን የማስታገስ አቅም ቢኖረውም በንጥረ ነገር የበለጸገ ባለመሆኑ በርካታ የጤና እክሎችን ይዞ ይመጣል።

  1. የተመጣጠነ ምግብ አለመውሰድ

ስኳር የበዛባቸውን እና በፋብሪካ በተደጋጋሚ ሂደት የተቀነባበሩ የምግብ አይነቶችን ማዘውተር አዕምሯችን እንደሚጎዱ ይነገራል። እንደ ፒዛ ያሉ እና ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸው ምግቦች እና መጠጦችን አብዝቶ መውሰድ ለከፍተኛ የደም ግፊት፣ ካንሰር፣ የልብ ህመም እና አዕምሮ መሳትም ያጋልጣል።

  1. ከንባብ መራቅ

በፈረንሳይ ብሄራዊ ኢንስቲትዩት የተደረገ ጥናት እንዳመለከተው ከንባብ መራቅ በአዕምሮ መሳት ህመም የመጠቃት እድልን በ18 በመቶ ያሳድጋል። የአዕምሮ መሳትያጋጠማቸው ሰዎች የንባብ ባህላቸው ዝቅተኛ ከሆነ ደግሞ አደጋው የከፋ እንደሚሆንም ነው ጥናቱ ያረጋገጠው። ማንበብ የአዕምሯችን የተለያዩ ክፍሎች ከማነቃቃትም ባለፈ ችግሮች ሲያጋጥሙን በንቃተ ለመፍትሄው እንድንዘጋጅም ያግዘናል። ባለሙያዎች እንደሚሉት በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል ማንበብ ምርጡ የመዝናኛ አይነት ነው። ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፤ ከማንበብ የምናገኘው እውቀትም ለችግሮቻችን ጋሻ ይሆናል።

ይሁን እንጂ በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶች ስክሪን ላይ ማለትም ኮምፒውተር ወይም ሞባይል ላይ ከማንበብ ይልቅ መጽሃፍትን በእጅ እያገላበጡ ማንበብ የአይን ጤናን ለመጠበቅ የራስ ምታት ህመምን ለመከላከል እንደሚረዳ ጠቁመዋል።

ሌሎች አዕምሮአችን የሚያውኩ መጥፎ ልማዶች

እንቅልፍ ማጣት፣ ቴሌቪዥን ላይ አፍጥጦ መዋል፣ ከፍተኛ የስራ ጫና እና የመዝናኛ ጊዜ እጦት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ሃሳብ እና አስተያየት ከመስጠት መታቀብ፣ ጭንቀት ማብዛት እና መሰል አጉል ልማዶችም አዕምሮአችን የማዛባት አቅማቸው በጣም ከፍተኛ ነው።

ስለሆነም በማወቅም ይሁን ቸል በማለት ከእነዚህ መጥፎ ልማዶች ጋር እየኖርን ከሆነ ብናስብበት መልካም ነው እንላለን።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.