ከፍተኛ የድምፅ ብክለት ለልብ ድካምና ለደም ግፊታ በሽታ ያጋልጣል

ከፍተኛ የሆነ የድምፅ ብክለት ለልብ ድካም፣ ለደም ግፊትና ተያያዥ በሽታዎች እንደሚያጋልጥ በአሜሪካ የልብ ማህበር አባላት ተመራማሪዎች ባካሄዱት ጥናት አረጋግጠዋል።

ከአውሮፕላን ማረፊያ ፣ከፈጣን የመኪና መንገዶች ፣ከፋብሪካዎች እና መሰል ተቋማት የሚወጡ ከፍተኛ ድምፆች

ለበሽታው መንስኤዎች መሆናቸው በጥናቱ ተገልጿል።

ከፍተኛ የድምፅ ብክለት አዕምሯችን ትክክለኛ ስራውን እንዳይሰራ በማወክ ለከፍተኛ ጭንቀት እና ድብርት ይዳርጋል።

ይህ ሁኔታም በሰውነታችን ውስጥ ያሉትን የደም ስሮች በማቁሰልና በማሳበጥ ትክክለኛ የሆነ የድም ዝውውር እንዳይካሄድ ምክንያት ይሆናል።

ይህ ዓይነቱ ሂደት በመጨረሻም ለከፍተኛ የልብ ድካም፣ለደም ግፊት እና ተያያዝ ለሆኑ በሽታዎች እንደሚያጋልጥ በጥናቱ ተመላክቷል።

በጥናቱ ከፍተኛ የድምፅ ብክለት ለልብ ድካም በሽታ ማጋለጡን ከማረጋገጥ ባለፈ፥ የድምፅ ብክለት ከሰው ልጆች የሰውነት ክፍል አወቃቀር ጋር ያለው ፊዚዮሎጂካል ግንኙነት ግልፅ አለመሆኑን የጥናቱ ተሳታፊ አዛር ራድፋር ተናግረዋል  ።

ይሁን እንጂ ጥናቱ በሁለቱ ክስተቶች መካከል ያለው ፊዚዮሎጂካል ግንኙነት ለማጥናት የመነሻ ሃሳብ በመሆን እንደሚያገለግል ተመራማሪው ጠቁመዋል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

2 Comments

  1. Tactile stimulation Design nasal Regurgitation Asymptomatic testing GP Chemical harm Force Second apparatus I Rem Behavior Diagnosis Hypertension Operation Nutrition Hybrid Treatment Other Inhibitors Autoantibodies essential aid Healing Other side Blocking Anticonvulsant Therapy less. best generic sildenafil Jykqbh jlsfnj

Comments are closed.