ወንዶች ከሴቶች በበለጠ ለቆዳ ካንሰር ይጋለጣሉ

ወንዶች ከሴቶች በበለጠ ለቆዳ ካንሰር እንደሚጋለጡ አንድ ጥናት አመላክቷል።

የቆዳ ካንሰር በሽታ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣ ሲሆን፥ ቀጥታ ቆዳን ለጨረር ማጋለጥ ለበሽታ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

በጥናቱ ወንዶች ከጨረር እራሳቸውን በመጠበቅ እና የቆዳ ካንሰረን በመከላከል ረገድ ያላቸው ግንዝቤ ውስን መሆኑም ነው የተመላከተው።

ከፈረንጆቹ 1985 እስከ 2015 ባሉት ተከተታይ ዓመታት በዓለም ጤና ድርጅት በ33 ሀገራት ላይ በተደረገ ጥናት የቆዳ ካንሰር ጋር በተየያዘ ከሴቶች የበለጠ ወንዶች ተጠቂ መሆናቸው እና ከዚሁ በሽታ ጋር በተያያዘ ይህወታቸው እንደሚያልፍ ተገልጿል።

በዚህም ከ2013 እስከ 2015 ባሉት ዓመታት ከ100ሺህ ወንዶች በአማካይ በአውስትራሊያ 5ነጥብ 72፣ በስሎቫኒያ 3ነጥብ86፣ በጃፓን 0ነጥብ 24 በመቶ ህይወታቸው ሲያልፍ ከዚሁ ተመሳሳይ የሴቶች ቁጥር በአውስትራሊያ 2ነጥብ 53፣ በስሎቫኒያ 2ነጥብ 58፣ በጀፓን 0ነጥብ 18 ያህል ሴቶች ከዚሁ በሽታ ጋር በተያያዙ የጤና ችግር ህይወታቸው ማለፉ ነው የተገለጸው።

በጥናቱ ከላይ በተጠቀሱት ተከታታይ ዓመታት በጃፓን በሁለቱም ፆታዎች ከዚሁ በሸታ ጋር በተያያዘ የተመዘገበው የሞት ምጣኔ ቅናሽ ያሳየ ቢሆንም፥ የወንዶች ቁጥር ከሴቶቹ ቁጥር ከፍ ማለቱ ታውቋል።

የጥናቱ ጸሃፊ ዶክተር ዶሮተይ ያንግ ወንዶች በምን ሁኔታ ለዚሁ ሽታ የመጋለጥ እድላቸው ከፍ እንዳል ሌሎች ተጨማሪ ጥናቶችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.