በጠዋት መንቃት ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል ተባለ

በጠዋት የሚነቁ ሰዎች በተለይም ሴቶች ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው የቀነሰ መሆኑን የብሪታኒያ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

የብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ የተመራማሪዎች ቡድን እንዳስታወቁት፥ ጠዋት መንቃት እና የጡት ካንሰረን ምን እንደሚያገናኛቸው ባይታወቅም፤ ጠቀሜታ እንዳለው ግን አረጋግጠናል ብለዋል።

በአግባቡ እንቅልፍ መተኛት ለሰው ልጅ የሚሰጠው ጠቀሜታን ለመለየት በተካሄደው ጥናት ነው ይህ ውጤት የተገኘውም ብለዋል።

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፥ ሁሉም የሰው የራሱ የሆነ የወስነት ሰዓት አለው፤ ይህ ሰዓትም ሰውነታችን በ24 ሰዓት ውስጥ እንዴት እንደሚሰራ የሚቆጣጠር ነው።

ከእነዚህም ውስጥ የጠዋት ሰዎች የሚባሉ አሉ የሚሉት ተመራማሪዎቹ፥ እነዚህ ሰዎች በጠዋት ከእንቅልፋቸው የሚነቁ ሁሉንም በአግባቡ ከውነው ምሽትም በጊዜ ድካም የሚሰማቸው ናቸው ብለዋል።

ተመራማሪዎቹም በዚህ ላይ በመመስረት መረጃዎችን የሰበሰቡ ሲሆን፥ በጥናቱ ላይም ከ2 ሺህ 300 በላይ ሴቶችን ዲ.ኤን.ኤ በመውሰድ ነው ጥናቱን ያካሄዱት።

በጥናቱም የጠዋት ሰዎች በሚለው ውስጥ የሚካለሉ ሴቶች ለጡት ካንሰር የመጋለጥ አድላቸው አነስተኛ ሆኖ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.