ከብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ አሜሪካ ትኩረቷን የቻይና ኩባንያዎች ላይ አድርጋለች

ከብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ አሜሪካ ትኩረቷን የቻይና ኩባንያዎች ላይ ማድረጓ አየተገለጸ ነው።

ሚሞሪ እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚያመርተው ፉጃን ጂንሁዋ የተባለው የቻይና ኩባንያ ለአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ስጋት መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፥ ከአሜሪካ ኩባንያውች ጋር ባለው ግንኙት ላይ ገደብ መጣሉ ተገልጿል።

ከዚህ በኋላም የአሜሪካ ኩባንያዎች ለዚህ ኩባንያ ምርቶቻቸውን ለማቅረብ ፈቃድ ማግኘት ያለባቸው መሆኑም ነው የተገለጸው።

ክስተቱ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከፈጠራ መብት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ በቻይና ላይ ቀደም ሲል ሲያነሱት የቆየውን ውንጀላ እና የንግድ ጦርነት ሊባብሰው አንደሚችል ተነግሯል።

የሀገሪቱን ደህንነትና ጥቅም የሚጻረሩ የውጭ ሀገር ኩባንያዎች ላይ አሜሪካ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ ደህንነቷን ለማረጋገጥ እንደምትሰራም የአሜሪካው የንግድ ሚኒስትር ውልበር ሮዝ ተናግረዋል።

ባሳለፍነው ዓመትም ዜድ.ቲ.ኢ የተባለው የቻይና ኩባንያ አሜሪካ በኢራን እና ሰሜን ኮሪያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በመተላለፍ ምክንያት ከአሜሪካ ኩባንያወች ጋር ያለውን ግንኙነት መቋረጡ የሚታወስ ነው።

በተመሳሳይ መልኩ የአውስትራሊያ መንግስት የሁአዌ እና ዜድ.ቲ.ኢ የገመድ አልባ በይነ መረብ አገልግሎት እንዳይሰጡ ሲያግድ የብሪታኒያ የመረጃ መረብ ጥቃት መካላከል ቡድን በበኩሉ የዜድ.ቲ.ኢ ኩባንያ የምርት ውጤቶች ለመረጃ መረብ ብርበራ የሚያጋልጡ ስለመሆናቸው መጠቁሙንም ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.