የፌስቡክ የእለት ጎብኚዎች ቁጥር ዝቅ ማለቱ ተነገረ

የፌስቡክ የእለት ጉኚዎች ቁጥር መቀነሱ እና ገቢውን ከተጠበቀው በታች መሆኑን ኩባንያው በቅርቡ ባወጣው ጥናት አመልክቷል።

ባሳለፍነው መስከረም ወር 1 ነጥብ 51 ቢሊየን ሰዎች ፌስቡክን በየእለቱ ይጎበኛሉ ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፤ ወደ ፌስቡክ ጎራ ያሉ ሰዎች ግን 1 ነጥብ 49 መሆኑ ነው የተነገረው።

የጎብኚዎች ቁጥር ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል የተባለ ቢሆንም፤ የጎብኚዎች ቁጥር ግን ከተጠበቀው በታች መሆኑ በሪፖርቱ ላይ ተመልክቷል።

የጉብኚዎች ቁጥሩ በአሜሪካ እና በካናዳ ምንም ጭማሪ ያላያሰ መሆኑ እና በነበረበት የቀጠለ ነው የተባለ ሲሆን፥ በአውሮፓ ግን በእጅጉ ቀንሷል ተብሏል።

ከገቢ ረገድም በፈረንጆቹ 2018 ሶስተኛ ሩብ ዓመት የኩባንያው ገቢ 13 ነጥብ 7 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መሆኑን እና ይህም በ33 በመቶ ከፍ ያለ ነው ያለው ኩባንያው፤ ሆኖም ግን በእቅድ ከተያዘው 42 በመቶ ዝቅ ያለ ነው ተብሏል።

ዋትስ አፕ እና ኢንስታግራም የተባሉ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ መተግበሪያዎች ባለቤት የሆነው ፌስቡክ፤ የጎብኚዎቹ እና የገቢው መጠን ከተጠበቀው በታች መሆኑን ተከትሎ ፊቱን ወደ እነዚህ መተግበሪያዎች ሊያዞር እንደሚችልም ተገምቷል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.