ፕሮጀክተር የተገጠመለት ስማርት ሰዓት – Smartwatch With Skin-Touch Projector!

የ                              

ቻይናው ሀይር ኩባንያ ፕሮጀክተር የተገጠመለት ስማርት የእጅ ሰዓት አስተዋውቋል።

ኩባንያው ስማርት ሰዓቱን በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው የሞባይል ኮንግረስ የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ ላይ ነው ይዞ የቀረበው።

ልክ እንደ ሌሎች ስማርት ሰዓቶች ሁሉ የጤና ሁኔታን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶች የሚሰጠው ይህ የእጅ ሰዓት፥ በላዩ ላይ ፕሮጀክተር ተገጥሞለታል ነው የተባለው።

ስማርት ሰዓቱ ላይ የተገጠመው ፕሮጀክተር እጃችንን ልክ እንደ ሌላ ተጨማሪ ስክሪን ሊያስጠቅመን የሚችል ነው።

በዚህም እንደ ፎቶግራፍ ያሉ ነገሮችን ጨምሮ ሌሎች ስማርት ሰዓቱ ላይ የምንጠቀማቸውን አገልግሎቶች ከፕሮጀክተሩ በሚወጣው ጨረር አማካኝነት በእጃችን ላይ መመልከት እንችላለን ነው የተባለው።

ሀይር ስማርት ሰዓት በቀጣይ ሶስት ወይም አራት ወራት ውስጥ በቻይና ውስጥ ለገበያ መቅረብ እንደሚቸምርም ተነግሯል።

ስለተቆረጠለት የመሸጫ ዋጋ ግን እስካሁን የተባለው ነገር የለም።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement