የአእምሮ ስራን ለማሻሻል የሚረዱ ተግባራት – Increasing Your Memory Power

                                       

አእምሯችን በርካታ ተግባራትን ከሚያከናውኑ ሰውነታችን ክፍሎች ውስጥ አንዱ እና ወሳኙ ነው።

ታዲያ ይህ የሰውነታችን ክፍል በምንከተለው የአኗኗር ዘይቤ፣ በአመጋገባችን እና በምናከናውናቸው ተግባራት ሊጎዳ እንደሚችል ይነገራል።

እንዲህ አይነት ተግባራት ደግሞ አእምሯችን ስራውን በአግባቡ እንዳይሰራ እንደሚያደርጉ ይታወቃል።

አእምሯችን ከዚህ አይነት ተጽዕኖ እንዲወጣ ለማድረግ እና የሚሰራውን ስራ ለማሻሻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምክሮች ጠቃሚ ናቸው።

የተመጣጠነ አመጋገብ

ለጤናችን ተስማሚ የሆኑ እና ተመጣጣኝ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ አጠቃላይ ጤንነታችንን በመጠበቅ አእምሯችን በቀላሉ እንደ መርሳት በሽታ ላሉ ችግሮች እንዳይጋለጥ ያደርጋል።

የአእምሮን ጤና ለመጠበቅ የሚረዱ ምግቦች፦

አትክልትና ፍራፍሬዎች፥ በቫይታሚን ኢ የበለፀጉ እንደ ቆስጣ እና ብሮኮሊ ያሉ ምግቦች እንዲሁም በቤታ ካሮቲን ንጥረነገረ የበለፀጉ እንደ በርበሬ እና ስኳር ድንች ያሉ ምግቦች ለአእምሮ ጤንነት ጠቃሚ መሆናቸው ይነገራል።

የአሳ ዘይት፥ በኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ንጥረ ነገር የአሳ ዘይት አእምሯችን ስራውን በአግባቡ እንዲከውን ከሚያደርጉት ውስጥ ይመደባል።

ለውዝ፥ በአንቲኦክሲዳንት ንጥረ ነገር የበለፀገውን ለውዝ መመገብም ለአእምሮ ጤንነት ጠቀሜታ እንዳለው ነው የሚነገረው።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ 

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አዘውትሮ መስራት አእምሯችን በቀላሉ ለመርሳት ችግር እና ሌሎች የጤና እክሎች እንዳይጋለጥ ይረዳል ተብሏል።

በቀን ውስጥ በትንሹ ለ30 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ ብቻው2ን አእምሯችንን በቀላሉ ስራውን እንዳይሰሩ ከሚያደርጉት እክሎች ለመከላከል በቂ መሆኑም ተነግሯል።

ከዚህ በተጨማሪ ሩጫ፣ የውሃ ዋና፣ ሳይክል መስራት እና መሰል የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎቸን አዘውትሮ መስራት የአእምሯችንን ጤና ለመጠበቅ ከሚመከሩት ውስጥ ይገኛሉ።

እነዚህን እና መሰል የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን አዘውትሮ መስራት አእምሯችን ሁሌም ንቁ እንዲሆን እንደሚያደርግ ነው የሚነገረው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement