የካንሰር የደም ምርመራ “አሰደናቂ ውጤት” አስገኘ – Cancer Blood Test ‘Enormously Exciting’

                                                           

ተመራማሪዎች በሕክምና ሳይንስ ትልቅ እመርታ ነው ያሉትን ለካንሰር አለም አቀፍ የደም ምርመራ እርምጃ ወሰዱ።

በጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ስምንት ተመሳሳይ ጠባይ ያላቸውን በሽታዎች መለየት የሚያስችል ሙከራ አድርጓል።

አላማቸው ካንሰርን ቀድሞ ማወቅና ሕይወትን ማዳን ነው፤ ምርምሩን የእንግሊዝ ባለሙያዎች “እጅግ በጣም አስደናቂ” ሲሉ ገልፀውታል።

እጢዎች አነስተኛ የሆነ የዘረመልና የፕሮቲን አሻራቸውን በደማችን ውስጥ ትተው ያልፋሉ።

የካንሰር ፍለጋው ምርመራ የሚመለከተው በተደጋጋሚ በካንሰር ወቅት የሚነሱ 16 ጅኖችንና ስምንት ፕሮቲኖችን ነው።

በዘር እንቁላል፣ ጉበት፣ ሆድ ጣፊያ፣ ጉሮሮ፣ ትልቁ አንጀት፣ ሳንባ፣ ጡት ካንሰር ባለባቸው እና ወደ ሌሎች ቲሹዎች ባልተዛመተባቸው 1005 ሕሙማን ላይ ሙከራው የተደረገ ሲሆን፤ በአጠቃላይ 70 በመቶ የሚሆነው ምርመራ ካንሰር መኖሩን ያሳያል።

የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ቤት ዶ/ር ክርስቲያን ቶማስቲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት “ይህ ቀድሞ የመለየት ምርመራ ወሳኝ ነው፤ ውጤቱም በጣም አስደናቂ ነው” ብለዋል።

“እንደሚመስለኝ ይህ ካንሰርን በማጥፋት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።”

ካንሰር ቀድሞ ከተገኘ ለማከም ያለው እድል ሰፊ ነው።

ምርመራ ከተደረገባቸው ከስምንት ካንሰሮች አምስቱ ቀድሞ የመለየት ምርመራ ፕሮግራም አልነበራቸውም። የጣፊያ ካንሰር አነስተኛ ምልክት ብቻ ስላለው ማወቅ የሚቻለው ከዘገየ በኋላ ስለሆነ ምርመራውን ካደረጉ አምስት ሕሙማን መካከል አራቱ በዛው አመት ይሞታሉ።

በቀዶ ጥገና ሊወገዱ የሚችሉ እጢዎችን ማግኘት ለህሙማኑ “የቀን እና የለሊት ያህል ልዩነት አለው” ይላሉ ዶ/ር ቶማስቲ።

“አሁን ካንሰር ሕመምን የመፈለግ ሙከራው የካንሰር ምርመራ አድርገው በማያውቁ ሰዎች ላይ ተሞክሯል።

“ይህ ከጠቃሚዎቹ ምርመራዎች መካከል አንዱ ይሆናል። ተስፋ የሚደረገው ለጡት ካንሰር የሚደረገውን ማሞግራም እና ለአንጀት ካንሰር የሚደረገውን ኮሎኖስኮፒ አይነት ሌሎች ምርመራዎችን ያግዛል ተብሎ ነው።”

ዶ/ር ቶማስቲ ለቢቢሲ እንደገለፁት “የደም ምርመራ በአመት አንዴ ይደረጋል ብለን ነው የምናስበው”

በካንሰር ላይ በርካታ ምርምር የሚያደርጉትና የቡድን መሪ የሆኑት ዶ/ር ገርት አታርድ ለቢቢሲ እንዳሉት “ይህ በጣም ትልቅ አቅም ነው። በጣም ተደንቄያለሁ። ያለ ስካን ወይንም ያለኮሎኖስኮፒ በደም ምርመራ ብቻ ካንሰርን መለየት መቻል ትልቅ ሚስጥርን እንደመፍታት ነው።”

አክለውም “” በጣም ተቃርበናል”ካንሰርን ለመመርመር የደም ናሙናን መፈተሽ የሚያስችል”ቴክኖሎጂውም አለን።”

ነገር ግን አሁንም ካንሰሩ ከተገኘ በኋላ ምን መደረግ አለበት የሚለው ላይ ጥያቄ አላቸው።

በአንዳንድ ሕመሞች የካንሰር ሕክምናው ከህመሙ ጋር ከመኖር የበለጠ በጣም ፈታኝ ነው።

ለምሳሌ ወንዶች የዘር ፍሬ ካንሰር ሲኖርባቸው ቀስ በቀስ ስለሚያድግ ከሚታከም ይልቅ በቅርበት የህክምና ክትትል ማድረግ ይመከራል።

“ካንሰርን በተለየ መልኩ ስናገኘው ሁሉም ሕክምና ያስፈልገዋል ብለን አንወስድም ” ይላሉ ዶ/ር አታርድ።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement