የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች መጠንቀቅ ያለባቸው ነገሮች

1.የአካል ጥንቃቄ፡-

 ጥፍር ሲቆረጥ የሰዉነት ስጋን በማይነካ መልኩ በጥንቃቄ መቁረጥ፡፡
 ሰፋፊ ጫማ ማድረግ/ በፊት ከሚያደርጉት አንድ ቁጥር ጨምሮ ማድረግ፡፡
 በባዶ እግር አለመሄድና እግርን የሚልጡ ጫማዎች አለማድረግ፡፡
 እግር ሲታጠቡ በቀዝቃዛ ዉሃ መታጠብ፡፡
 እግራቸው ላይ በየጊዜው ቁስለት መኖሩንና አለመኖሩን መከታተል፡፡
 በተለያየ ምክንያት እግራቸው ላይ ቁስለት ከተፈጠረ እንደ ሌሎች ሰዎች ቶሎ
ስለማይድን ወደ ህክምና መሄድ፡፡

2.መድሃኒት

 ከሀኪም ቤት የሚሰጠዉን መድሃኒት በተሰጠው ትዕዛዝ ከተወሰደ ሰዉነት ዉስጥ ያለዉን ግሉኮስ ከሚገባ በላይ ከፍ እንዳይል በማድረግ በሽታው በልብ፤ኩላሊት ና ሌሎች አካላት ላይ የሚያደርሰዉን ችግር እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡

3.ምግብ፡-
 የስኳር ይዘት ካላቸው እንደ፡-ሻይ፤ለስላሳ መጠጦችና ወዘተ መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ አንዳንዴ ስኳር አብዝቶ በመብላት የስኳር በሽታ ይይዘናል ብለው የሚያስቡ ስህተት ነው፡፡በስኳር በሽታ ከተያዝን ግን መብላት የለብንም፡፡

 ስብና ቅባት የበዛበትን ከመመገብ መቆጠብ፡- ይህም ምግቡ በልብና የደም ስሮች ላይ ችግር ስለሚያመጣና በተለይም የስኳር በሽታ ላለባቸው ደግሞ ይብስባቸዋል፡፡
 በተለያየ ምክንያት ከሰዉነት ዉስጥ የስኳር መጠኑ መዉረዱን የሚያሳየው ላብ፤ ድካምና የልብ ምት በፍጥነት በሩጫ ላይ እንዳለ ሰው የሚመታና እራሱን የሚስት ከሆነ ቶሎ የስኳር ይዘት ያለውን ምግብ ትንሽ መውሰድ አለባቸው፡፡

ይህ ምልክት ታይቶ ከተስካከለ ቦኃላ ግን እንደ ከረሜላ፤ ለስላሳ ወዘተ ምግቦች ማቆም አለብን፡፡

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement