6ቱ ተልባን ከመመገብ የሚገገኙ ጥቅሞች – 6 Health Benefits Flax

                                               

  1:ከፍተኛ የአሰር መጠን አለ

ተልባ ሞሚ እና ኢሞሚ የሆኑ ቃጫዎችን በውስጡ በከፍተኛ መጠን የያዘ ሲሆን ይህም አንጀት ላይ ያሉ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ያስወግዳል፤ሰውነታችን ውስጥ ያሉ ጮማዎችንም ይቀንሳል

2.ኮልሰትሮልን ይቀንሳል
ተልባ በውስጡ በሚገገኛ omega 3 አማካኝነት መጥፎ ኮልሰትሮል (low density lipoprotein,LDL)እንዲቀንስ ያደርጋል በዚህም የልብ እና የደም ግፊት በሽታ ተጋላጭነትንም ይቀንሳል፡፡

3፡ካንሰርን ይከላከላል
በJournal of clinical cancer research ላይ እንደታተመው የተልባ ፍሬ የጡት ካንሰር ተጋላጭነት እንደሚቀንስ አውጥቶል፡፡በተልባ ፍሬ ውስጥ የሚገኙት 3ቱ ሊጋኖች በአንጀት ላይ በሚገገኙት ባክቴርያዎች አማካኝነት ወደ ኢንትሮላክቶን እና ኢንትሮሲኮል በመቀየር ሰውነት ውስጥ ያሉ ሆርሞኖችን እንዲመጣጠኑ ያረጋል

4፡ኦሜጋ 3ን (alpha linolenic acid) 
-በውስጡ ስለያዘ በሽታን የመከላከል አቅምን እንዲገነባ ይረዳል
-የልብ ምት እንዲስተካከል እና የልብ ጡንቻ መቆጣት እንዳይኖር ይረዳል፡፡
-በማረጥ ጊዜ ያለ ህመምን ይቀንሳል፡፡
-በተጨማሪ የወር አበባ ኡደትን ያስተካክሉ፡፡

5-ቁርጠትን እና የሆድ መነፋትን ይቀንሳል፡፡

6፡-የአጥንት መገጣጠሚያ (ቁርጥማት) ህመሞችን ያስታግሳል 
-በውስጡ ኦሜጋ 3 ስለያዘ ነጭ የደም ሴሎች በብዛት እንዲመረትና ህመሙ እንዲቀንስ ይረዳል፡፡

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

 

 

Advertisement