የአሳ ዘይትን የመመገብ የጤና ጥቅሞች – Health Benefits Of Fish Oil

                                                        

*በአየር ብክለት ምክንያት የሚመጡ ችግሮችን ይከላከላል

በኦሜጋ 3 የበለፀው የአሳ ዘይት በአየር ብክለት ምክንያት ሊከሰቱ ከሚችሉ የልብና ተያያዥ ህመሞች የመከላከል አቅም አለው።

*የመገጣጠሚያ ህመም ስሜትን ማስታገስ
የመገጣጠሚያ ህመም ካለዎት ሁለት የሾርባ ማንኪያ የአሳ ዘይት በቀን መውሰድ የህመም ስሜትዎን በግማሽ እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ።

*የእርጅና ምልክቶችን ይቀንሳል
የአሳ ዘይትን መጠቀም ከእድሜ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሁኔታዎች የመቀነስ ጥቅም አለው።

*ስብን በፍጥነት ያቃጥላል
የአሳ ዘይት ስብ በፍጥነት እንዲቃጠል ስለሚያደርግ ተመራጭ ነው።
*የአንጎልን የተግባር ሀይል ይጨምራል የማስታወስ ችሎታንም ያግዛል

*ለጡንቻ ጤናማነት ጠቃሚ ነው

*የአጥንትን ጤናማነት ይጨምራል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ጤናማ አጥንትን ለመስራት ኦሜጋ 3 አስተዋፅዎ ያለው ንጥረነገር ነው። የአሳ ዘይትን ከመጠቅም ባለፈ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ የአጥንት መሳሳትን መከላከል ያስችለናል።

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement