SPORT: አስደንጋጭ ዜና– አይቮሪኮስት ተጫዋቿን በልብ ህመም ሜዳ ላይ በሞት ተነጠቀች

በቻይና ሲጫወት የነበረው የቀድሞ የኒውካስትሉ አማካይ ቼክ ቲዮቴ በልብ ህመም ሜዳ ላይ ወድቆ ህይወቱ ካለፈ በኋላ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አይቮሪኮስት በተመሳሳይ የልብ ህመም ሜዳ ላይ ሌላኛውን ተጫዋቿን በሞት ተነጠቀች።

 የቀድሞ የአሴክ ሚሞሳክ ተጫዋች የነበረው ኢውግን ኮፊ ኩዋሜ ኩማሲ ስታድየም ላይ በነበረ ጨዋታ ላይ ተዝለፍልፎ በመውደቅ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

 በምስራቅ አፍሪካ ላይ ይበልጥ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው ሶካ ኢስት ባወጣው መረጃ መሰረት ተጫዋቹ ከጓደኞቹ ጋር በመጫወት ላይ እያለ ተዝለፍሎ ሜዳ ላይ ወድቋል።በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ለማትረፍ የተደረገው ሙከራ ውጤታማ ሳይሆን ቀርቷል።

 ክለቡ የቱርኩ እጊሪዲስፓር ኢውግን ኮፊ ኩዋሜ በልብ ህመም በመጠቃቱ ሜዳ ላይ ወድቆ ህይወቱ ማለፉ በማሳወቅ ለቤተሰቦቹ መጽናናትን በመመኘት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

 አይቮሪኮስት በቻይና ቤጂንግ ኢንተርፕራይዝ ይጫወት የነበረው ቼክ ቲዮቴን በልምምድ ላይ ሜዳ ላይ ወድቆ ህይወቱ ካለፈች ከወር በኋላ ኢውግን ኮፊ ኩዋሜ ሌላኛው አይቮሪኮስታዊ ሜዳ ላይ ህይወቱ ያለፈች ተጫዋች መሆን ችሏል።

 አፍሪካ በተመሳሳይ የልብ ህመም ተጫዋቾቿ እየተቀጠፉ መሄዳቸው የቀጠሉ ሲሆን ይህንን ለመቆጣጠር ፊፋ አዲስ መመሪያ ለማውጣት እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

ምንጭ: ዕዮብ ዳዲ

ethioaddissport.com

 

 

 

Advertisement