በጥልቀት የመተንፈስ ዋና ጠቀሜታዎች – The Benefits of Deep Breathing

                                                         

በተለምዶ ከእንቅስቃሴዎች ውስጥ እንደ አንዱ ስለማንቆጥረው በጥልቀት የመተንፈስ ጥበብን በየቀን ልምዳችን ላንተገብረው እንችላለን፡፡
በHealth digest ድረ-ገፅ ላይ በወጣው ጥናት በጥልቀት የመተንፈስ ጥበብ በርካታ ጠቀሜታዎችን እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡ ልምዱ በተለይ በማለዳ ቢሞከር ደግሞ ውጤታማነቱ እጥፍ ይሆናል ተብሏል፡፡
• የመዝናናት ስሜትን አንድም ለአእምሮአችን በሌላ በኩል ደግሞ ለሰውነታችን በቀላሉ ይሰጣል፡፡ አንዳንዴ ሰውነታችን መጨናነቁን ላናስተውል እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ሰውነታችንን ስንታጠብ፣ ለስላሳ ሙዚቃዎችን ስናዳምጥና በአልጋችን ላይ እረፍት ስናደርግ ትንፋሽን ከሆዳችን ለማውጣት እየሞከርን ብንተነፍስ ለውጡን በቀላሉ ማየት እንችላለን፡፡
• ውጥረት ሊይዘን በሚችልበት ሁኔታ ላይ ስንሆን ለምሳሌ በሆስፒታል ውስጥ ሆነን ውጤት ስንጠብቅ፣ እጅግ የበዛ ትኩረት የሚጠይቅ ስብሰባ/ስራ ላይ ስንሆን እንደ ጥያቄና መልስ ያሉ ውድድሮች ላይ ስንሳተፍ በጥልቀት የመተንፈስ ጥበብን በተገቢው መልኩ መተግበር ይመከራል፡፡


• እንደ አስምና ብሮንካይት አይነት የመተንፈሻ ህመም ያለባቸው ሰዎችም ቢጠቀሙበት ሳምባቸው በቂ ኦክሲጅን እንዲያገኝና ጤና እንዲሆኑ አጋዥ ነው፡፡
• የሜዲቴሽን/ተመስጦ ውጤታማነት በትክክል መስራትና መታየት እንዲችልም አጋዥ ነው፡፡
• በተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ላይ በቂ አቅም እንዲኖረን፤ የመደብነውን እንቅስቃሴ ያለድካም በሰዓቱ መጨረስ እንድንችልም ጠቃሚ ነው፡፡
• ሰውነታችንን ሊመርዝ የሚችልን ካርቦን ዳይኦክሳይድን አብዝተን በማውጣታችንም ጤናማ መሆን እንችላለን፡፡
• ለደም ዝውውር ጤናማነት፤ ለጤናማ የምግብ መፈጨት ስርአትና በሽታን የመቋቋም አቅምን ለመጨመርም አይነተኛ ሚና ይጫወታል ሲል Health digest አስነብቧል፡፡

ምንጭ፡- Health digest Lov

Advertisement