ለጤናማ ትዳር 14 ጠቃሚ ምክሮች

                                      

ትዳር ከተባረከ በአለም ካሉ የከበሩ ስጦታዎች ሁሉ ትልቁ ስጦታ ነው፡፡ ጥንዶች አስበውትም ሆነ ሳያስቡት የሚያደርጓቸው ጥቃቅን ስህቶች ግን ትዳርን ገነትም ሆነ ሲዖል ሊያደርጉት ይችላሉ ስለዚህ እነዚህን ነጥቦች ልንጠቁማችው ወደድን

1) ትዳርን እንደ ከባድ ስራ አትቁጠሩት፡- ነገሮች ሁሉ ጭንቅላት ውስጥ ነው የሚጠናቀቁት ትዳርህን /ሽን እንደ ስራ ወይም እንደ ግዴታ ሳይሆን ስንወጣ በናፍቆት እንደሚጠብቀን የምንወዳት/ደው አጋር ያለበት ምርጥ ቦታ እንደሆነ አስብ/ቢ፡፡
2) አጋርህን/ሽን በሰዎች ፊት በምንም ሁኔታ ክብሯ/ን የሚነካ/የሚያሳንስ ነገር አታድርግ፡፡
3) ስለ ባልሽ/ሚስትህ ደካማ ጎን ለቤተሰብህም ሆነ ለጓደኞችህ/ሽ አትንገር/ሪ፡፡
4) አጋርህን/ሽን በምንም አይነት መልኩ ከማንም ጋር አታነጻጽሪ/ር፡፡
5) በቤት ውስጥ ስራዎች ውስጥ ለመተጋገዝ ሞክሩ መተጋገዙና አብሮ ማብሰሉ የበለጠ እንድትቀራረቡና እንድትተሳሰቡ ያደርጋቸዋል፡፡
6) በመሀከላችው አለመግባባት ሲፈጠር እርስ በእርስ ከመወነጃጀል አንዳችው በዝምታ ለማሳለፍ ይሞክሩ፡፡
7) ‹‹ትዳር ይቅርታንና እሺታን ፤ ዝምታንና ችሎ ማለፍን የምንለማመድበት ጥሩ ትምህርተ ቤት ነው›› ፡፡
8) ፍቅራችሁን በቁሳዊ ነገሮች አትለኩት ከቤት ፤ከንብረት ከሀብት ሁሉ በላይ አብራችው መሆናችውን አስቡ፡፡
9) ወደፊት ስለሚኖራችውና እንዲኖራችው ለምትፈልጉት ነገር በማውራትና በመነጋገር አንድ የጋራ ህልምና ፍላጎት እንዲኖራችው አድርጉ ፡፡
10 ) በህይወታችው ለሚከሰቱ ነገሮች ሁሉ በጋራና በመተሳሰብ ለመወሰን ይሞክሩ፡፡
11) ኩርፊያና መሰዳደብን ያስወግዱ፡፡
12) ጓደኞችዋ/ቹ ጋ ያለሽን/ህን ቀረቤታ በልክ አድርጊ/ግ፡፡
13) ከመጋባታችው በፊት እንደሚያደርጉት ስጦታቸውንና ልዩ የፍቅር ቃላትን ይለዋወጡ፡፡
14) በተቻለ መጠን በልጆቻችው ወይም በቤት ውስጥ አብረው በሚኖሩ ሰዎች ፊት ስለትዳር አጋርዎ መጥፎነት አያውሩ ፡፡ 

ምንጭ:- አዲስ አድማስ

Advertisement