በየቦታው በቅሎ የምናየውን አጠ ፋሪስ ወይም አስተናግሮ ምን ያህል ያውቁታል?

                                       

በአማርኛ አጠ ፋሬስ፣ በኦሮምኛ ማንጂ፣ በሳይናሳዊ ስሙ ደግሞ ዳቱራ ስትራሞኒየም( Datura stramonium) ይባላል:: በእሾኽ የታቀፉ ፍሬዎች ያሉት ሲሆን ጠንከር ያለ ሽታ አለው:: ቁመቱ እስከ 2 ሜትር ሊያድግ ይችላል:: በኢትዮጵያና በሌሎችም የከፍታ መጠናቸው ከ600-2800 ሜትር በሆኑ አካባቢዎች እዚህም እዚያም በቅሎ ይታያል:: ይህ ተክል ለእንስሳት መርዛማ በመሆኑ አይመገቡትም:: ነገር ግን በባሕል ሕክምና ቅጠሉ ለራስ ምታት ጥቅም ላይ ይውላል:: የተቀቀሉ ፍሬዎቹ ደግሞ ከጥርስ ህመም እፎይታ ለማግኘት ያገለግላሉ፡፡ጡንቻን ዘና የማድረግ ባሕሪም ስላለው ለሕመም ማስታገሻ ህክምና ይሆናል:: ለሳል ለሚወሰድ ሽሮፕ መድኃኒትም እንደ አንድ ግብዓት ያገለግላል:: ከትንፈሳ ስርዓት ጋር ለተያያዙ የጤና ችግሮች በተለይ ለአስም በሲጋራ መልክ ይወሰዳል:: አጠ ፋሪስ ልክ እንደ አልኮል ሰውነትን ዘና የማድረግ ባሕሪ ስላለው ሰዎች እንደመዝናኛ ፈታ ለማለትም ይጠቀሙታል:: በተለይ በገጠሩ ክፍሎች፡፡ የዚህ ተክል የደረቀ ቅጠል ያለው የኬሚካል ግ’ንብ ውህድ ትሮፔን አልካሎይድ ሃዮሳያሚን (tropane alkaloids hyoscyamine ) (70%)፣ ስኮፖላሚን( scopolamine) (20%) ነው፡፡ ልይ አትሮቲን (atropine hyoscyamine) በአንዳንድ ኬሚካሎች ስንመረዝ ለማርከሻ መድኃኒትነት ይወሰዳል፡፡ እንዲሁም ያለፍቃዳችን ለሚያጋጥም የጡንቻ መሸማቀቅና መኮማተር መድኃኒትነት የሚያገለግል ሲሆን የዓይን ሕክምናም ላይ አስተዋጽኦ አለው፡፡ በተጨማሪም ለፓርኪንሰን በሽታና በጉዞ ወቅት ለሚያጋጥም ሕመም( motion sickness) ለሚሆኑ መድኃኒቶች ጥቅም ይሰጣል፡፡

ምንጭ:- አዲስ ጤና

Advertisement