በቆዳዎት ላይ ያለ ሸንተረር ምቾት ነስቶት ይሆናል። ሸንተረሩን የሚያስወጡ ሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ከእርግዝና እና ከውፍረት በኋላ ያለው የሰውነት መቀነስ ነው፡፡ እነዚህ ምልክቶች በእግር፣ ክርን፣ ወገብ፣ ጡት እና ጀርባ ላይ ሊወጡ ይችላሉ፡፡ ይሄን ለማጥፋት ግከገበያ ተገዝተው ከሚመጡ ይልቅ በቤት ውስጥ የተሰሩ መድሀኒቶች ሁነኛ መፍትሄዎች ናቸው::
የእንቁላል (ነጭ) ፈሳሹ ክፍል፦ ይህ የእንቁላል ፈሳሽ በፕሮቲን የበለጸገ ነው። በዚህ ምክንያትም በቆዳችን የሚገኝን ሸንተረር ለማጥፋት በጣም ይረዳል፡፡ እንቀላሉን ከመቀባታችን በፊት ሸንተረር ያለበትን በማጠብ ቆዳችንን ንጹህ ማድረግ ይኖርብናል። ከዚያም ሁለት እንቁላል ወስደን አስኳሉን ከፈሳሹ በመለየት የእንቁላሉን ፈሳሽ ክፍል በሹካ በደንብ አማስለን ካበቃን በኋላ መቀባት፡፡ የእንቁላሉ ፈሳሽ እንዲደርቅ ቢያንስ ለ20 ደቂቃ እንተወው። ከዚያም በኋላ መታጠብ እና ብንችል የወይራ ዘይት ቆዳችንን መቀባት። ይህን ማድረግ ቆዳችን እንዳይደርቅ ያግዛል። ይህን ዘዴ ቢያንስ ለሁለት ሳምንታት በየቀኑ መጠቀም ውጤቱን አስተማማኝ ያደርገዋል።
ይሞክሩት፤
በእርግጠኝነት ጥሩ ውጤት ያገኛሉ፡፡
ምንጭ: mahderetena