የጥፍራችን ቅርጽ ስለባህሪያችን ምን ይላል? አስገራሚ ነገር ይመልከቱት

 ተተርጉሞ የተጻፈው፦ በሙለታ መንገሻ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 23፣ 2007 (ኤፍ. ቢ. ሲ) የእጅ ጣታችን ጥፍር ቅርጽ ስለኛ ባህሪ ይናገራሉ ይባላል።

ይህንን ለማወቅም በምስሉ ላይ ካሉት የጥፍር ቅረጾች ውስጥ ከኛ ጋር ተመሳሳይ ሆነውን በማመሳከር ከስር የተዘረዘሩትን ባህሪችንን ማወቅ እንችላለን።

ከኛ ጥፍር ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን የጥፍር ቅርጾች ምስል ካላገኘንም በምስሉ ላይ ከጣታችን ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው ምስሎች ጋር በማመሳል ማወቅ እንችላለን።

1 ረዘም ብለው የሬክታንግል ቅርጽ ያላቸው ጥፍሮች

ረዘም ብሎ ሬክታንግል የጥፍር ቅርጽ ያላቸው ሰዎች በባህሪያቸው ጥሩ የሚባል ማህበራዊ ግንኙነት ያላቸው እና ከሰዎችም ጋር በቀላሉ ሊግባቡ ሚችሉ ናቸው።

ፈጣን አእምሮ፣ አዳዲስ ግኝቶች መፍጠር የሚያስደስታቸው እና አዳዲስ ጓደኞችን በቀላሉ ማፍራት መቻላቸውም ከባህሪቸው ውስጥ የሚጠቀስ ነው።

የሚሰሩትን ስራም ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ያከናውናሉ ይባላል።

2 ሰፋ ያለ ጠፍጣፋ የጥፍር ቅርጽ

እንዲህ አይነት የጥፍር ቅርጽ ያላቸው ሰዎች ባለ ንጹህ አእምሮ እና ሰዎች የሚንግሯቸውን ነገሮችን አስተውለው ማዳመጥ ከባህሪቸው ውስጥ ይጠቀሳል።

ከመናገራቸው በፊትም የሁሉንም ሰዎች ሀሳቦች በደንብ ማዳመጥ እና ከዳመጡ በኋላ በቂ ጊዜ ወስደው አስበው መናገርም በህሪያቸው ነው።

የሰዎችን ባህሪም በቀላሉ መረዳት ይችላሉ።

ውስብስብ ለሆኑ ችግሮች እና ጉዳዮችም ምርጥ መላምት እና ሀሳቦችን በማፍለቅ እንዲሁም መፍትሄ በማፈላለግ የሚያክላቸው የለም ይባላል።

3 አጠር ብሎ ክብ ቅርጽ ያለው ጥፍር

አጠር ብሎ ክብ ቅርጽ ያለው ጥፍር ያላቸው ሰዎች የፈጠራ ችሎታቸው ከፍተኛ ከሚባሉ ሰዎች ይጠቀሳሉ።

እንዲሁም ለሰዎች ቀና የሆነ አመላካከት ያላቸው ሲሆን፥ በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ማስደሰትም ከባህሪቸው አንዱ ነው።

ለሚወዷቸው ሰው ታማኝ ሲሆኑ፥ የሚወዱትን ሰው መንከባከብ እና ማስደሰትም ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ ነው።

ያሰቡትን ነገር ከማድረግ እና ህልማቸውን ከማሳካት ምንም ሊያቆማቸው አይችልም።

እንዲህ አይነት ቀርጽ ያለው ጥፍር ያላቸው ሰዎች አልፎ አልፎ የግትርነት ባህሪ የሚታይባቸው ሲሆን፥ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግን ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው ይባላል።

4 ያልተስተካከለ እና በጣም አጭር ጥፍር ያላቸው

ያልተስተካከለ እና በጣም አጭር ጥፍር ያላቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ጥፍራቸውን በጥርሳቸው የመቆራረጥ ባህሪ ያላቸው ሲሆኑ፥ ለአዳዲስ ነገሮች ለዩ ስሜት ያላቸው እና አሮቆ አሳቢ ናቸው።

ለአዳዲስ ጓደኞቻቸው የተለየ እንክብካኬ የመስጠት አመል አላቸውም ይባላል።

በሚናደዱበት ጊዜም ንዴታቸውን በመቆጣጠር ለሰዎች ያልተናደዱ መስለው የመታየት ልምድም ይስተዋልባቸዋል።

ነገሮች ምንም ያክል መራራ ቢሆኑባቸውም እውነትን ከመናገር ወደኋላ አይሉም።

5 ተለቅ ብሎ የሬክታንግል ቅርጽ ያለው ጥፍር

የሚሰሩትን ስራ በሙሉ ሀላፊነት መስራት፣ ነገሮችን ማስተባበር እና መምራት፣ ታታላቅ ውሳኔ የሚሰጡባቸው ስብሰባዎች ላይ መካፈል ተለቅ ብሎ የሬክታንግል ቅርጽ ጥፍር ያላቸው ሰዎች ባህሪ ነው ይባላል።

ለሚሰሩት ስራ ትክረት የሚሰጡ እና ለሚሰሩበት ድርጅት በጎ አመላካከት ያለቸው ነውም ይባላሉ።

6 ሶስት ማእዘን ቅርጽ ያለው ጥፍር

ሶስት ማእዘን ቅርጽ ያለው ጥፍር ያላቸው ሰዎች የሚሰሩት ስራ ላይ ተነሳሽነት ማሳት እና ቆራጥነት ከባህሪቸው ውስጥ የሚጠቀስ ነው።

የሚሰሩትን ስራም በትኩረት የሚሰሩ ሲሆን፥ አብዛኛውን ስራቸውንም በስኬት የሚያጠናቅቁ ናቸው።

7 ሞላላ ሆኖ ረዘም ያለ ጥፍር

የፈጠራ አቅማቸው ከፍ ያለ መሆኑ የሚነገርላቸው ሞላላ እና ረዘም ያለ ጥፍር ቅርጽ ያላቸው ሰዎች፥ በጣም እድለኛ እና በውብ ነገሮች ተከበቡ ናቸው ይባላል።

እንዲሁም አዳዲስ ፈጠራ ያለበትን ስራ ደከመኝ ሳይሉ እና ሳይሰላቹ የመስራት አቅማቸውም ከፍ ያለ ነው።

ሌሎች ሰዎች ለመጥቀም በሚሰራው ስራም ከምንም በላይ የሚያስድስታቸው እና በትጋት የሚሰሩት ስራ ነው።

ምንጭ፦ http://www.mahderetena.com

Advertisement