ምግባችን ያክመን

ለመድሀኒትና ለህክምና የምናወጣው ገንዘብና ግዜ የህይወታችንን ሰፊ ድረሻ ይዛል፡፡ ምግባችንን እንደመድሀኒት ካልወሰድን መድሀኒትን እንደ ምግብ የምንወስድበት ግዜ ይመጣል ፡፡ ይህንን ለማስተካከል ደግሞ ግዜው አሁን ነው ፡፡ ከምግቦች የምናገኘውን ጥቅም ለማወቅ ይረዳችው ዘንድ ይህን ጽሁፍ እንሆ ብለናል፡፡

1. ፓፓያ

  • የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል
  • የቆዳ ድርቀትን ይከላከላል
  • ፓፓያን በቀጥታ ቆዳዎን በመቀባት ወይም በመመገብ የሚያምር ለስላሳ ቆዳን መጎናፀፍ ይቻላሉ
  • የተፈጨ ፓፓያ የተሰነጣጠቀ ተረከዝን ለማከም ይጠቅማል
  • ተፈጥሮአዊ የሞቱ ሴሎችን ከቆዳ ላይ ማስወገጃ መንገድ ነው
  • የቆዳን ተፈጥሮአዊ ቀለም ለመመለስ ይረዳል
  • ለሆድ ትላትል ህክምናነት ይጠቅማል
  • ጥቁር ነጠብጣቦችን ለማስወገድ በቆዳ ላይ የሚታዩ የእርጅና ምልክቶችን ለመቀነስና ለማከም ይረዳል
  • ራሰ በራነትን ይከላከላል፣ የፀጉር እድገትንና ጥንካሬን ይጨምራል

2. ሎሚ

  • ጸረ­ባክቴሪያ ባህሪ አለው
  • በቫይታሚን ሲ የበለጸገ ነው
  • የሎሚ ጭማቂ በውሃ ቀላቅሎ መጠጣት ሰውነታችን የአሲድ አልካላይን ሚዛኑን ለመጠበቅ ይረዳዋ
  • የጉበትን ስራ በማነቃቃት ዩሪክ አሲድና ሌሎችንም ጎጂ ንጥረነገሮች ከሰውነታችን ውስጥ ለማስወገድና የሀሞት ፈሳሽንም የፈሳሽነት ባህሪውን እንዳያጣ ያደርጋል
  • የሎሚ ጭማቂ በቫይታሚን ፒ የበለጸገ እንደመሆኑ ከህዋሳት መጎዳትና በእድሜ መጨመር ሳቢያ የሚከሰቱትን ʻፍሪ ራዲካሎችʼን ለማስወገድ ይረዳል
  • የሎሚ ጭማቂ ጸረ­ካንሰር ባህሪያት አሉት
  • ከእድሜ መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የመገጣጠሚያ አካላት በሽታን ይከላከላል
  • በሎሚ ውስጥ ያለው ፔክቲን ፋይበር የመጥፎውን ኮልስትሮል መጠን ከመቀነሱም በላይ የመጥገብ ስሜትን ስለሚፈጥር በብዛት ከመመገብ ያግዳል

3. ሃባብ

  • ለሰውነት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ቪታሚኖችን፣ ማዕድንና ሳይበዛ ለሰውነት በሚያስፈልግ መጠን ካሎሪንም የያዘ ተወዳጅ ፍራፍሬ ነው ።
  • ውፍረት ለመቀነስ ይረዳል
  • ከስኳር በሽታ
  • ከልብ ህመም ችግር
  • ለሰውነት ተጨማሪ ሃይል መስጠት
  • ለጤናማ የጸጉር እድገት
  • ለጤናማ የምግብ መፈጨት ስርአት እና የሰውነት ድርቀትን ለመከላከል ይረዳል
  • ደም ግፊት
  • ሃባብን መመገብ ሌላው ጠቀሜታው ከጉልበት በታች የሚከሰትን ከፍተኛ የሆነ የደም ዝውውር ወይም ግፊትን ማስወገድ መቻሉ ነው።ለካንሰር፣ ሰውነት ላይ የሚፈጠሩ አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስወገድ በሚረዱ የቪታሚን ሲ አይነቶች የበለጸገው ሃባብ ሌላኛው ጠቀሜታ የካንሰር ተጋላጭነትን መቀነስ መቻሉ መሆኑን ይኼው ጥናት ያሳያል

4. ቃርያ

  • ቫይታሚን ኤ ዋነኛ ከሚባሉ ቃርያ ውስጥ ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች ስለሆነ እና ለአይን ጥራት እና ጤናማነት ከፍተኛ ሚናን ስለሚጫወት ቃርያን መመገብ ጠቀሜታን ይሰጣል።
  • ቃርያ በቫይታሚን ሲ እጅግ የበለጸገ በመሆኑ ቆዳችንን ጤናማና የሚያበራ እንዲሆን ያደርጋል
  • በሽታን የመከላከል አቅምን ማዳበር
  • የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናል
  • ጉንፋን፣ሳል፣እንዲሁም የሳንባ ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው
  • ለአጥንት ጤናማነት እና ጥንካሬ እጅግ ጠቃሚም ነው
  • ለሰውነታችን ጠቃሚ ያልሆኑ ንጥረነገሮችን በማስወገድ እና የፋይበር ምንጭ በመሆን የሆድ ድርቀትን ይከላከላል
  • ቃርያን የሚመገቡ ሰዎች የቆዳ መሸብሸብ እንዳይኖራቸው እንዲሁም ቶሎ እንዳያረጁ ያደርጋል።

5. አቮካዶ

  • በሰውነታችን የሚገኝን የኮሌስትቶል መጠን ዝቅ በማድረግ ረገድ አቻ የለውም፣
  • በውስጡ ያዘለው ቫይታሚን ኢ ለልብ ህመም/ስትሮክ የመጋለጥ ዕድላችንንም በእጅጉ ይቀንሳል
  • እርጅናን ለመከላከል እና የቆዳ ውበት ተጠብቆ እንዲቆይ ይረዳሉ
  • በአቮካዶ ውስጥ በብዙ መጠን የሚገኘው አንቲ ኦክሲዳንት ቆዳ እንዳይሸበሸብ እና የሞቱ የቆዳ ሴሎች እራሳቸውን እንዲተኩ ሲያግዝ፥ ካሮቲኖይድስ የተባለው ንጥረ ነገርም በቆዳ ላይ የሚታዩና የቆዳን ውበት የሚቀንሱ ምልክቶች እንዳይከሰቱ ያደርጋል
  • ክብደት ለመቀነስ ፍቱን ነው
  • ለስኳር ህመምተኞች ተመራጭ ነው፣ በአቮካዶ ውስጥ በጥሩ መጠን የሚገኘው ፖታሺየም በደማችን ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን በማመጣጠን በሰውነት ውስጥ የልብ ስራንና የስኳር መጠንን የተረጋጋ እንዲሆን ያስችላል።

6. ቀይ ሽንኩርት

  • የሰውነትን ከበሽታ የመከላከል አቅም ያሳድጋል
  • በውስጡ ክሩሚየም የተባለ ንጥረነገር አለው። ይህ ንጥረነገር የደም ግፊትንና ስኳርን ይቆጣጠራል
  • ቀይ ሽንኩርት ገላን የማሳከክና የማቃጠል አይነት ባህሪ ያላቸውን አለርጂዎች ይቆጣጠራል
  • ቀይ ሽንኩርት ጥሬውን መመገብ ኮሊስትሮንን ከመቆጣጠሩ ባሻገር የጤናማ ልብ ባለቤት ያደርጋል
  • ክዩርስቲን የተባለው በቀይ ሽንኩርት ውስጥ የምናገኘው ንጥረነገር ካንሰርን የመከላከል ሚና አለው
  • በንብ በምንነደፍበት ጊዜ ትንሽ የቀይ ሽንኩርት ውሃ ብንቀባ ከስቃዩ እፎይታን እናገኛለን
  • ቀይ ሽንኩርት በየእለቱ መጠቀም ከጨጓራ አልሰር ይጠብቃል
  • አረንጓዴ ጫፍ ያለው ለጋ ቀይ ሽንኩርት የቫይታሚን ኤ ይዘቱ ከፍተኛ በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው።

7. ድንች

  • ለጨጓራ ህመም ፈውስ
  • ለደምግፊት
  • ለካንሰር
  • ለኩላሊት
  • ለራስምታትና ለሌሎችም
  • በተጨማሪም የድንች ጭማቂ በተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማሻሻል፣ በየጊዜው የሚከሰትን የራስ ምታት ህመምና የወር አበባን ተከትሎ የሚከሰቱ ህመሞችን ለማስታገስ ይረዳልም::

ምንጭ: ዶክተር አለ

Advertisement