በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙ ኢንፌክሽኖች በጨቅላ እድሜ ወቅት በሚኖር የአንጎል እድገት ላይ ተፅእኖ አለው – ጥናት

              

በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥም ኢንፌክሽን ወይም የነብሰጡር እናቷን በሽታ የመከላከል አቅም የሚጎዳ ህመም በምትወልደው ህፃን የአንጎል እድገት ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ።

በብራድልይ ፒተርሰን የሚመራው የሎስ አንጀለስ የልጆች ሆስፒታል የጥናት ቡዱን፥ በእርግዝና ወቅት በሽታን የመከላከል አቅም የሚያዳክም ኢንፌክሸን በህፃኑ አእምሮ ጤንነት ላይ የአጭር ወይም ረዥም ጊዜ አሉታዊ ተፅእኖን ያሳድራል።

ኢንፌክሽን፣ ጭንቀት፣ ሕመም ወይም አለርጂ የመሳሰሉ በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም ለማዳከም መነሻ ምክንያቶች ሊሆኑ እንደሚችሉም ተጠቁሟል።

በሰውነት ውስጥ በሚገኘው በሽታን የመከላከል አቅም ከነዚህ መነሻ ምክንያቶች ውስጥ አንዱን ሲታይበት፥ ኢንፌክሽን እንደሚታይ ተገልጿል።

ጥናቱ ወጣት ሴቶችን በመመልመል በስድስተኛው የእርግዝና ወር ደም በመውሰድ፣ በዘጠነኛው ወር ያለው የጨቅላው የልብ ምት በመከታተል ለጥናቱ ተጠቅሟል።

በተጨማሪም የጨቅላ ሕፃናት የአንጎል ክፍል በማንበብ እና ህፃናቱ በ14 ወር እድሜ ላይ ያላቸው ባህሪን ግምገማ አካቷል።

ከዘጠኝ ወር እናቶች የተወሰደው ደም በአይ ኤል-6 እና ሲ አር ፒ (CRP) የደም ደረጃ መለክያዎች የተፈተነ ሲሆን፥ ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅም በትክከል በሚሰራበት ጊዜ ወይም ባልተዳከመበት ወቅት ኤል-6 እና ሲ አር ፒ በከፍተኛ መጠን ተገኝቷል።

በተጨማሪም ቡድኑ ለአንጎል ነርቭ ግንባታ አመላካች ነው ያለው የልብ ምት ክትትል አድርጓል።

የቡድኑ የምርመራ ውጤት ሲ አር ፒ ከህፃናት የልብ ምት መለዋወጥ ጋር ተዛማጅነት እንዳለው ያሳየ ሲሆን፥ ይህም የእናቶች ህመም የህፃኑ የአዕምሮ እድገት ቅርፅን በሚጀምርበት ጊዜ እንደሚጀምር አመላካች ነው ብለዋል።

በአጠቃላይ ይህ ጥናት የሚያመለክተው በእናት ደም ውስጥ ያሉ ኢንፌክሽኖች በህፃናት አጭር እና ረጅም ጊዜ የአአምሮ ለውጦች ተያያዥነት እንዳለው ተመልክቷል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement