የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው ራሳቸውን በቤት ውስጥ የሚንከባከቡ ሰዎች ማድረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ምንድናቸው?

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ የጤና ተቋማትን ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ለማዋል የተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የቫይረሱን ምልክቶች የማያሳዩ እና ቫይረሱ ህመም የማይፈጥርባቸው ሰዎች የአኗኗራቸው ሁኔታ ታይቶ በቤታቸው ቆይተው ራሳቸውን እንዲንከባከቡ የማድረግ አሰሰራር እየተተገበረ ይገኛል።

ታዲያ እነዚህ ራሳቸውን በቤት ውስጥ የሚንከባከቡ ሰዎች ቤት ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ ማድረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ምንድናቸው?

ከፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የኤካ ኮተቤ የትምህርት እና ስልጠና ክፍል ባልደረባ አቶ ይስሃቅ ብርሃኑ ታማሚዎች ቤት ውስጥ እንዲቆዩ እና ራሳቸውን እንዲንከባከቡ የሚደረገው መጀመሪያ ይህንን ማድረግ እንደሚችሉ ሲረጋገጥ መሆኑን አንስተዋል።

እንዲሁም የቫይረሱን ቀጥተኛ ምልክት ማለትም ማስነጠስ፣ ማሳል እንዲሁም ሌሎች ምልክቶችን የማያሳዩ መሆን አለባቸው ነው ያሉት።

በጥቁር አንበሳ ስቴሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ክፍት ባልደረባ ዶክተር ኤፍሬም ሃይሌ በበኩላቸው፥ ምንም እንኳ መጀመሪያ ቫይረሱ ምልክቶችን አያሳይ እንጂ ቀስ በቀስ ምልክቶችን እያሳየ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ቫይረሱ ያለባቸው እና እራሳቸውን በቤት ውስጥ የሚንከባከቡ ሰዎች የቀን ተቀን ለውጦቻቸውን ሊከታተሉ ይገባል ብለዋል።

ምልክቶችን ካዩም መደናገጥ ሳይሆን ለህክምና ባለሞያዎች ማሳወቅ እንደሚገባ  ነው የተናገሩት።

እነዚህ ባለሙያዎች እንዳሉትም ራስን ከመንከባከብ ባሻገር በቂ እረፍት ማድረግ፣ ፈሳሽ ነገሮችን ባግባቡ መውሰድ፣ የአካል ብቃት አንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጤናማ አመጋገብን መከተል በተለይም በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ፣ ፍራፍሬዎችን ማዝወተር ፣ ስጋን አብስሎ መመገብ፣ቀዝቃዛ ምግብ እና መጠቶችን ማስወገድ  እንደሚያስፈልግ መክረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ቫይረሱ ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ ከሌሎች የቤተሰባ አባላት ጋር ያለን ንክኪ ማስወገድ፣ የጋራ መጠቀሚያዎች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ፣ ከቤት እንስሶች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣ ለራስ የተዘጋጀ ክፍል ውስጥ በጥንቃቄ መቀመጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምንጭ: FANA

Advertisement

10 Comments

Comments are closed.