ናሳ የማርስን ውስጣዊ አወቃቀር ለማጥናት ሮቦት ላከ

የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ኤጀንሲ ናሳ ከሰባት ደቂቃ መንጠር በኋላ የላካት ሮቦት በቀይዋ ፕላኔት ወይም ማርስ ላይ በሰላም አርፋለች።

ዘ ኢንሳይት ፕሮብ የተባለችው ይህች ሮቦት አላማ አድርጋ ያነገበችውም የማርስን ውስጣዊ አወቃቀር ጥናት ለማድረግ ነው።

ማርስ ላይ ጥናት ሲደረግ ከመሬት ቀጥሎ ሁለተኛ ፕላኔት ያደርጋታል።

የሮቦቷም ማርስ ላይ ማረፍ የተሰማው ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ይህም በጭንቀት ሲጠብቁ ለነበሩት ከፍተኛ እፎይታን ፈጥሯል።

በናሳ ካሊፎርኒያ ጄት ፕሮፐልሺን ላብራቶሪ ተሰስብበው የነበሩ ሳይንቲስቶችም ሮቦቷ ማርስ ላይ በሰላም ማረፏን ሲያዩ በደስታ እንደፈነጠዙ ተዘግቧል።

የናሳ ዋና አስተዳዳሪ ጄምስ ብሪደንስታይን “የሚያስገርም ቀን ነው” ባሉት በዚህ ዕለት ደስታቸው ከፍተኛ እንደሆነም ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንደደወሉላቸውም ጨምረው ገልፀዋል።

የካሊፎርኒያ ጄት ፕሮፐልሺን ላብራቶሪ ዳይሬክተር ማይክ ዋትኪንስ በበኩላቸው “ይህ ስኬት ሁላችንንም ሊያስታውሰን የሚገባው ደፋርና የተለያዩ ቦታዎችን ልናስስ እንደሚገባን ነው” ብለዋልPresentational white space

ኢንሳይት ሮቦት በአሁኑ ወቅት ኤልሲየም ፕላኒሺያ በተባለው ሰፊ ሜዳማ ቦታ ያረፈች ሲሆን ይህም ከቀይዋ ፕላኔት (ማርስ) ምድር ወገብ ተጠግታ መሆኑም ተገልጿል።

ሮቦቷ ከማረፏም በፊት ናሳ ቦታውን በማርስ ትልቁ የፓርኪንግ ቦታ ሲል ጠርቶታል።

ወዲያው ሮቦቷ እንዳረፈች በደቂቃ ውስጥ በሮቦቷ የተነሳው ፎቶ ደብዘዝ ያለ ቢሆንም በኋላ ግን ጥርት ያለ ፎቶ መላኳ ተዘግቧል።

ሮቦቷ የመጀመሪያዋ ምርምር የሚሆነው የማርስ ውስጣዊ አወቃቀርን ማጥናት ይሆናል።

በዚህም ጥናት ድንጋዮች ከምን እንደተሰሩ፣ የፕላኔቷን የሙቀት መጠንና እንዲሁም ማርስ በፈሳሽ ወይም በጠጣር የተሞላች ፕላኔት ነች ለሚለው ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል።

ኢንሳይት

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.