የኩላሊት ጠጠር ህመምና አመጋገብ

የኩላሊት ጠጠር በሽታ ከ 10 ሰው አንድ ሰው ላይ በህይወት ዘመኑ ሊከሰትበት የሚችል በሽታ ነው፡፡የኩላሊት ጠጠር በሽታ በጣም ትናንሽ የሆኑና ጠንካራ የሆኑ ጠጠሮች ሲሆኑ በኩላሊት ውስጥ በመጠራቀም የተለያዩ ማዕድናት ጨው መጠንን በመጨመር የሽንትን መጠን ይቀንሳሉ፡፡በመሆኑም የአመጋገብ ለውጥ በማምጣት የኩላሊት ጠጠርን መቀነስ ይቻላል፡፡

ለኩላሊት ጠጠር በሽታ እንደመንስዔ የሆኑ የአመጋብ ሁኔታዎች
ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን ምግቦች
ከፍተኛ የሆነ የሶዲየም አወሳሰድ
ዝቅተኛ የሆነ የፈሳሽ አወሳሰድ መኖር
ከፍተኛ የሆነ የኦክሳሌት መጠን የያዙ ምግቦችን በብዛት መመገብ፡፡

ለውዝ፣ቀይስር እና ስፒናሽ በውስጣቸው ከፍተኛ የሆነ የኦክሳሌት መጠን በመያዛቸው ለካልሺየም ኦክሳሌት የኩላሊት ጠጠር ያጋልጣሉ ይህ ማለት ግን እነዚህን ምግቦች ሙሉ በሙሉ ከምግባችን ውስጥ ማስወገድ አለብን ማለት አይደለም ግን ስንመገብ በመጠኑ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም በጣም ከፍተኛ ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች ደግሞ ለካልሺየም ፎስፌት ጠጠር ያጋልጣሉ፡፡እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የሶዲየም አወሳሰድና ዝቅተኛ የፈሳሽ አወሳሰድ ለዩሪክ አሲድ እና ሳይቲን ጠጠር ያጋልጣል፡፡

አመጋገብን በተመለከተ
የኩላሊት ጠጠር በሽታ እንዳይዘን ከተያዝንም ለመቆጣጣር እነዚህን ማድረግ አለብን እነሱም በብዛት ውሃ መጠጠት
የጨው አወሳሰድን መቀነስ ከእንሰሳት ተዋጽኦ የሚገኙ ፕሮቲኖችን መቀነስ ምክንያቱም እነዚህ ምግቦች በብዛት ከተመገብን ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ ዕድላችን ይጨምራል፡፡ በመሆኑም ከእጽዋት የሚገኙ ፕሮቲኖችን በብዛት መመገብ ለምሳሌ ባቄላ፣ምስር፣አኩሪ አተር፣ አተር እና ሽንብራ የመሳሰሉትን መመገብ ያስፈልጋል፡፡
የኦክሳሌት ንትረ ነገር በውስጣቸው በብዛት ያለባቸውን ምግቦች መቀነስ፡፡ በካልሺየም የበለጸጉ ምግቦችን በብዛት መመገብ ለምሳሌ ወተትና የወተት ተዋጽኦች
አትክልትና ፍራፍሬዎችን በብዛት መመገብ በተለያም የሚኮመጥቱ ፍራፍሬዎችን በውስጣቸው ቫይታሚን ሲ የያዙትን መመግብ የኩላሊት ጠጠርን ለመቀነስ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡

በውስጣቸው ብዙ ኦክሳሌት ንጥረ ነገር ያላቸውን ምግቦች ለምሳሌ ቀይስር እና ስፒናሽ ምግቦችን በካልሺየም ከበለጸጉ ምግቦች ጋር መመገብ የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር ይረዳል ምክንያቱም ካልሺየም ከኦክሳሌት ጋር አንጀታችን ውስጥ በመጣበቅ ጠጠር እንዳይፈጥር ስለሚያደርግ ነው፡፡

ዶክተር አለ በሁሉም የጤና ዘርፎች ላይ በብቁ ባለሙያዎች ለጤናዎ የሚበጅዎትን በቤትዎ ሆነው እያገለገልዎት ይገኛል፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

4 Comments

Comments are closed.