የክብደቷን አርባ እጥፍ የምትሸከመው አነስተኛዋ በራሪ ሮቦት

የስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ተማራማሪዎች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻሻለ ሁኔታ የክብደቷን 40 እጥፍ ዕቃ የምትሸከም አነስተኛ በራሪ ሮቦት መስራታቸውን አስታወቁ፡፡

ይህቺ ሮቦት ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሚለያት በሷ መጠን ካሉት ሮቦቶች ይልቅ ማንኛውም ቦታ መግባት ስለምትችል ነው ብለዋል፡፡

አነስተኛዋ ሮቦት ዕቃዎችን ከማጓጓዝ በተጨማሪ ነገሮችን የመግፋትና የመሳብ ክህሎት እንደተሰጣትም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ለአያያዝ ምቹ የሆነችው አነስተኛ ሮቦት በሮችን መክፈት እና መዝጋት እንደምትችል ተመራማሪዎቹ በምስል አስደግፈው አቅርበዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ “ፍላይክሮተግስ” የሚሏት ይህቺ አነስተኛ ሮቦት ከዚህ ቀደም በዚሁ ላብራቶሪ ውስጥ የተሰራችውን በማሻሻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሮቦቷ በመጠን አነስተኛ መሆኗና የመጠኗን ብዙ ክብደት መሸከም መቻሏ ለነፍስ አድን ስራዎች አመቺ እንድትሆን ያስችላታል ተብሏል፡፡

ተመራማሪዎቹ አክለውም እስከአሁን የነበሩት ሮቦቶች የክብደታቸውን ሁለት እጥፍ ብቻ ይሸከሙ እንደነበር አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.