በራሂ /ጂን/ ለማስተካከልና ለማርም የሚያስችለው አዲስ ቴክኖሎጂ

                   

ራሂን/ጂን/ ለማስተካከልና ለማረም ያስቻለው አዲሱ ቴክኖሎጂ ወደፊት በዘረመል የሚመጡ አንዳንድ በሽታችን ለማከም እንደሚያስችል አንድ አዲስ ጥናት አመልክቷል።

የአልበርታ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች በስነ-ህይወት ማሽን በመታገዝ ባካሄዱት ጥናት በሰው ልጆች ሴሎች ውስጥ የተከሰቱ የበራሂ ችግሮችን የማስተካከልና የማሻሸል ስራ እንደሰሩ ነው የተገለጸው።

 በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ የፈጠራ መብት ባለቤትነት ፈቃድ የወሰዱ ሲሆን፥ የጥናቱን ውጤት ከመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ጋር በመስራት አገልግሎት ላይ የማዋል ፍላጎት እንዳላቸውም ታውቋል ።

በጥናቱ የተገኘው ውጤት ለጡንቻና ደም መፍሰስ ችግሮች እና ለካንሰር ህሙማን መድሃኒት እንደሚሆንም በዘገባው ተገልጿል።

ቀደም ሲል በዚሁ ጉዳዩ ላይ የተለያዩ የጤና ምህንድስና የበራሂ አወቃቀርና ሂደት ላይ የማሻሻያ ጥናቶች ተደርገው እንደ ነበርም ተመራመሪዎቹ ገልጸዋል።

በዚሁ ጥናት በራሂዎች ‘‘ባክቴሮፌጂስ’’ ከተባሉ አጥቂዎቻቸው እራሳቸውን ለመጠበቅ ባክቴሪያ የሚፈጥሩና ባክቴሪያዎችም ቀድሞ ስለተፈጠረው ጉዳት መረጃ እንዲሰበስቡም ተደርጓል ተብሏል።

በአጥቂዎች የተወረረውን ዘረመል በመቁረጥ ጥቃቱን ማስወገድ እንደተቻለም ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ። 

በዚህም መንገድ በሰዎች አካል ውስጥ የተወሰኑ ‘‘ዘረመሎችን’’ ቆርጦ በማውጣት በራሂዎች ላይ የተፈጠሩ ጉድለቶች ማረምና ማስተካከል እንደተቻለም ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል።

ይሁን እንጂ ጤናማ በራሂዎችን ችግር ካለበቸው በትክክል ለመለየት ሊያስቸግር እንደሚችል ነው በዘገባው የተጠቆመው።

የጥናቱ ተመራማሪዎች ግን ትክክለኛውንና መስተካከል ያለባቸውን ዘረ መሎች ለማግኘት እንደቻሉና ጉድለት ያለባቸውን ‘‘ዘረመሎች’’ ቆርጦ በማውጣት የተሻለ ውጤት እንደተገኘ ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡ ነው በዘገባው የተገለጸው።

የሰው ልጅ ከትሪሊየን ያህል ሴሎች የተገነባ መሆኑ እና በራሂ/ጂን/ የማስተካከል ስራ ቋሚ መሆኑ አሁን ከተሰራው ጥናት አንፃር ካንሰርን የመሳሰሉ አደገኛ በሽታዎች ሲያጋጥሙ ከፍተኛ ትዕግስት የሚጠይቅ ስራ የሚጠብቅ መሆኑንም ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement