የአልኮል መጠጥ በተጎነጨን ቁጥር እድሜያችንን እያሳጠርን መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ

                     

በብሪታንያ ካንብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ አዲስ ጥናት ውጤት በቀን አንድ ግዜ አልኮል መጠጣት እድሜን ያሳጥራል ብለዋል ተመራማሪዎች።

600 ሺህ ጠጪዎች ላይ በተሰራው በዚህ ጥናት በሳምንት ከአምስት እስከ 10 ጊዜ የአልኮል መጠጥ የሚወስዱ ሰዎች ቢያንስ ስድስት ወራትን ከዕድሜያቸው ላይ እንደሚቀንሱ ገልጸዋል።

በሳምንት ውስጥ 18 ጊዜ የአልኮል መጠጥ የሚወስድ ሰው በህይወቱ ላይ አምስት ዓመታትን ሊያሳጥር ይችላል ይላል የጥናት ውጤቱ።

ከ19 አገራት የተውጣጡ ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት ጀምሮ ያሉ ጠጪዎች የተካተቱበት ጥናት እንደሚይሳየው 12 ነጥብ አምስት ዩኒት ወይንም አምስት ከባለ 175 ሚሊ ሊትር ብርጭቆ በላይ አልኮል የሚጠጡ ሰዎች ሞታቸውን እንደሚያፋጥኑ ገልጿል።

ነገር ግን ይላሉ ተመራማሪዎች፥ በየትኛውም ደረጃ ያለ የመጠጥ አወሳሰድ ከልብ ጋር ለተገናኙ በሽታዎች ለህመም የማጋለጥ ዕድሉ የሰፋ ነው ይላሉ።

በሳምንት 12 ነጥብ አምስት ዩኒት አልኮል የሚጠጡ ጠጪዎች 14 በመቶ በስትሮክ፣ 9 በመቶ በልብ ድካም በሽታ የመያዝ እንዲሁም ደምን ወደ ሰውነታችን የሚያሰራጨውን ህዋስ የመጉዳት እድል አላቸው ብለዋል ተመራማሪዎቹ።

በሌላ ዴንማርክ በተደረገ ጥናት በሳምንት ሶስትና አራት ጊዜ መጠጣት በዓይነት 2 የስኳር በሽታ የመያዝ ዕድልን ይቀንሳል ይላሉ።

በብሪታኒያ በ2016 በተደረገ ጥናት ጠጪዎች ከ14 ዩኒት በላይ መጠጣት እንደለሌለባቸው ወይንም በሳምንት 6 ጊዜ የአልኮል መጠጥ መውሰድ እንደሌለባቸው ተገልጿል።

በጣሊያን፣ ፖርቹጋል እና ስፔን ሰዎች በሳምንት እንዲጠጡ የሚመከረው ከዚህም በ50 በመቶ እንደሚልቅ የገለጹ ሲሆን፥ በአሜሪካ ደግሞ ለወንዶች ከነዚህም ይበልጣል ነው የተባለው።

ቀደም ያሉ ጥናቶች ቀይ ወይን መጠጣት ለልባችን መልካም መሆኑን ቢገልጹም፥ ሌሎች ተመራማሪዎች ደግሞ ይህ እጅግ የተጋነነ ሐሳብ ነው ብለዋል።

በካንብሪጅ ዩኒቨርስቲ ጥናቱን የመሩት ዶክተር አንጄላ ውድ የጥናቱ ዋና አላማ ሰዎች መጠጥ የሚወስዱ ከሆነ መጠኑን እንዲቀንሱ ለማሳሰብና ከልብ በሽታ ለተገናኙ በሽታዎች በህመም የመጋለጥ እድላቸውን እንዲቀንሱት ለመምከር ነው ብለዋል።

Advertisement