አዲስ ልብሶች አገልግሎት ላይ ከመዋላቸው በፊት መታጠብ አለባቸው፦ ጥናት

                    

አዲስ ልብሶችን ሳይታጠቡ መልብስ በባክቴሪያ ለሚተላለፉ በሽታዎች እንደሚያጋልጥ ተገለጸ።

በኒዩዮርክ ዩንቨርሲቲ የማይክሮ ባዮሎጂና የሴል ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ፕሊፕ ቴርኖ እንደሚሉት አዲስ ልብሶች አገልግሎት ላይ ከመዋላቸው በፊት መታጠብ አለባቸው።

 ልብሶቹ ለሽያጭ ሲቀርቡ በሳምንታት ውስጥ በርከት ያሉ ደንበኞች እንደሚሞክሯችውና ሳይገዟቸው እንደሚሄዱ ነው የተገለጸው።

 

ልብሶቹ የሚሸጡበት ጊዜ ፍጥነት፣ የልብሱ ማቆያ ጥበትና ስፋት ሌሎች ሁኔታዎችም የራሳቸው አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም ደንበኖች አዲስ ልብሶችን የመልበስ ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ በተደጋጋሚ እንደሚሞከሯቸው ታውቋል።

ፕሮፌሰር ፕሊፕ ቴርኖ በአልባሳት መደበሮች ላይ ባካሄዱት ጥናት የአልባሳት ደንበኞች ልብሶችን በመለካትና ሳይገዙ በመሄድ ባክቴሪያና ‘‘ጀርሞችን’’ ልብሶቹ ላይ ትተው እንደሚሄዱ አረጋግጠዋል።

በጥናቱ ለተለያዩ በሽታዎች መነሻ የሆኑ ባክቴሪና ‘‘ጀርሞች’’ በልብሶች ላይ እንደተገኙ ነው ፕሮፌሰር ቴርኖ ያረጋገጡት።

ሰዎቹ ‘‘በጀርም’’ና ቫክቴሪያ የተበከሉ ልብሶችን በመነካካት አፍ፣ አፍንጫ፣ ቆዳና ሌሎች የሰውንት ክፍሎችን በመንካት ልብሶቹ ለበሽታ መተላለፊያ መንገዶች እንደሆኑ በጥናቱ ተጠቅሷል።

በዚህ መንገድ የሚከሰተው አደጋ ቀለል ያለ ቢሆንም የመቁስልና የቆዳ መሰንጠቅ ችግር ባለባቸው ሰዎች ላይ ጉዳቱ ከፍ ሊል እንደሚችል ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል።

ከዚህም ሌላ በልብሶች ምርት ሂደት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የቀለምና ሌሎች ‘‘ኬሚካሎችም’’ ቆዳን የማቃጠል ስሜት ስልሚኖራቸው ልብሶችን አጥቦ መልበስ አስገዳጅ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ ነው ጥናቱ የሚጠቁመው።

በኒውጀርሲ የቆዳ ሃኪም የሆኑት ዶክተር መጋሀን ፈለይ አንዳንድ የልብስ ንጽህና መስጫዎች የሚጠቀሟቸው የማጽጃ ኬሚካሎች ውህድ ንጥረ ነገሮችና ቀለሞች ለተወሰነ ጊዜ ቆዳን ማቃጠልና ሽፍታ የሚያጋልጡ መሆኑን ነው የሚገልጹት።

ከኮፍያ ጀምሮ አዲስ ልብሶችን እንደየ ስሪታቸው ባህሪ በማጠብ ማድረቅና መጠቀም የእራስንና የሌሎችን ጤና መጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

ከመልበሻ ክፍል እንደወጣን ከመመገብ፣ መጠጣትና ሌሎች ተግባራትን ከማከናዎናችን በፊት እጃችንን በመታጠብ በልብሶች ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታወችን በቀላሉ መከላከል እንደሚሚቻል በዘገባው ተገልጿል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement