የጥርስ መቦርቦርን ለመከላከል – To Prevent Tooth Decay

                                           

ምግብ ከተመገቡ በኋላ አፍን አለመጉመጥመጥ እና አለማጽዳት የምግብ ቅሪቶች በጥርስ ላይ እንዲቀሩ ያደርጋል።

ይህ ሁኔታ ደግሞ ባክቴሪያና አሲድን በማብዛት በሂደት የጥርስ መጎዳትና መበስበስና ያስከትላል።
በዚህ መልኩ ነገሮች ከቆዩና እልባት ካላገኙ ደግሞ ጥርስን እስከማሳጣት ይደርሳሉ።
በተለይም በካርቦ ሃይድሬት የበለጸጉ እና ስኳር የበዛባቸውን ምግቦች ከተመገቡ በኋላ ጥርስን በአግባቡ ማጽዳትና መቦረሽን አይዘንጉ።
ዳቦ፣ ወተት፣ ፍራፍሬዎች፣ ኬክ እና እንደ ከረሜላ ያሉ ነገሮችን ከተመገቡ በኋላ ጥርስዎን በደንብ ያጽዱ።
የህክምና ባለሙያዎች ደግሞ የጥርስ መጎዳትና መበስበስን ለመከላከል የሚረዱ መንገዶችን ይጠቁማሉ፤
ጥርስን ፍሎራይድ ባላቸው የጥርስ ሳሙናዎች በቀን ሁለት ጊዜ መቦረሽ፤ ይህን ከምግብ በኋላም ቢያደርጉት።
በጥርስ መሃል ያሉ ቦታዎችን በንጹህ ጠንካራ ክር ማጽዳት (ፍሎስ) ማድረግ፤
ባክቴሪያዎችን የመግደል አቅም ባላቸውና የአፍ ውስጥ ኢንፌክሽንን ለመከላከል አፍን ለብ ባለ ጨዋማ ውሃ መጉመጥመጥ፤
አመጋገብን ማስተካከል እንደ ከረሜላ ያሉ ጣፋጭ ነገሮችን መቀነስ እና ከተቻለ ማስወገድ፤
ከተመገቡ በኋላ ሁልጊዜም ጥርስን ማጽዳት አይርሱ።
በተቻለ መጠን የጥርስ ህክምና ባለሙያዎችን ማማከርና ምክረ ሃሳቦችን መቀበልም ለጥርስዎ ደህንነት ይጠቅምዎታልና ይጠቀሙበት።
ከዚህ ባለፈም ከምግብ በኋላ ማስቲካ ማኘክ የጥርስን ደህንነት መጠበቂያው አንደኛው መንገድ ነውና ይጠቀሙበት።
ምክንያቱም ማስቲካ ባኘኩ መጠን በአፍ ውስጥ የሚመነጨው ምራቅ ባክቴሪያዎችንና ጥርስ ላይ የሚለጠፉ የምግብ ቅሪቶችን ለማስወገድ ይረዳልና።

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement