በኮምፒዉተር አማካኝነት ከሚመጣ የዓይን ውጥረት ለመገላገል 5 እርምጃዎች – Computer Eye Strain

በአሁኑ ጊዜ ብዙዎቻችን ስራ ቦታ ኮምፒዉተር መጠቀም የተለመደ ሆኗል፡፡ በመሆኑም በኮምፒዉተር አማካኝነት የሚመጣ የዓይን ውጥረት (Computer Eye Strain) ችግራችን ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከሆነ የዓይን ድካም/ ውጥረት ወይም ሌላ የዕይታ ህመም ከ50 እሰከ 90 በመቶ ለሚሆኑ ስራቸውን ኮምፒዉተር ላይ ባደረጉ ሰራተኞች የሚስተዋል ሲሆን ከቀላሉ የዓይን መቅላት ጀምሮ እሰክ የአካል ድካምና ሥራ ላይ ስህተት እስከመፈጸም የሚያደርስ ችግር ያስከትላል፡፡

ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ፭ እርምጃዎችን በመውሰድ በኮምፒዉተር አማካኝነት የሚመጣን የዓይን ውጥረት ለመከላከልና ሌሎችን በተለምዶ የኮምፒውተር ራዕይ ሲንድሮም (computer vision syndrome – CVS) ለመቀነስ ይቻላል፡፡

1. አጠቃላይ የዓይን ምርመራ ያድረጉ:

በኮምፒዉተር አማካኝነት የሚመጣን የዓይን ውጥረት ለመከላከል ከሚጠቅሙ ዋና ዋና ነገሮች መካከል አጠቃላይ የዓይን ምርመራ ማድረግ አንዱ ነው፡፡

2. ተገቢዉን የብርሃን/ነጸብራቅ መጠን ይጠቀሙ፡

የዓይን ውጥረት ብዙ ጊዜ የሚከሰተው ከፍተኛ ከቤት ዉጭ በደማቅ የፀሐይ ብርሃን ወይም ቤት ውስጥ በሚበራ አንጸባራቂ መብራት አማካኝነት ነው፡፡ ስለሆነም ኮምፒዉተር በሚጠቀሙበት ጊዜ ነጸብራቁን (brightness) የጽሑፍ መጠን (Text size) and እና ንጽጽር (contrast)

ማስተካከል ይኖርብዎታል፡፡ የአይን መነጽር የሚያደርጉ ከሆነ ጸረ-ነጸብራቅ (anti-reflective AR) ሽፋን ያለው መነጽር መሆኑን ያረጋግጡ፡፡

3. የኮመፒዉተር ማሳያዉን (display) ደረጃ ያሻሽሉ፡

የዱሮዉን ቱቦ መሰል ማሳያ/ሞኒተር (Cathode Ray Tube -CRT) የሚጠቀሙ ከሆነ በአዲስ ጠፍጣፋ-ፓነል ፈሳሽ ክሪስታል (flat-panel liquid crystal display – LCD) ማሳያ መተካት ይኖርብወታል፡፡ አዲስ ጠፍጣፋ ፓነል ማሳያ (LCD) ለመግዛት በሚመርጡበት ጊዜ በተቻለ መጠን ማያ ገጹ (highest resolution) ከፍተኛ ጥራት የሆነውን ይምረጡ፡፡ በተጨማሪም ዴስክቶፕ ኮምፒውተርዎ ቢያንስ 19 ኢንች መጠን ያለው ቲሆን ይመረጣል፡፡

4. ቶሎ ቶሎ ዓይዎን ያርገብግቡ፡

ኮምፒውተር የሚሰራ ሰው አይኖቹን ማርገብገብ ወይም ብልጭ ድርግም ማድረግ የአይን ድርቀት እንዳይከሰት ስለሚረዳን በኮምፒዉተር አማካኝነት የሚመጣን የዓይን ድካም/ ውጥረት ለመከላከል በጣም ወሳኝ ነው፡፡.በተጨማሪም ተገቢዉን እረፍት ማድረግና አይዎን ማሰራት ወይም ማንቀሳቀስ ይኖርብዎታል፡፡ ለምሳሌ የአይንዎን ድካም ለመቀነስ 20 ደቂቃዎች ያህል ኮምፒዉተር ላይ ከሰሩ በኋላ ከእርስዎ ቢያንስ 20 ጫማ (6 ሜትር) ርቀት ላይ የሚገኝ የሆነ ነገር ላይ ለ20 ሰከንዶች ይመልክቱ፡፡ ምክንያቱም ራቅ ያለ ነገርን ማየት የአይን ጡንቻ ድካምን በመቀነስ ዘና ስለሚያደርግ ነው፡፡ ይህንን እንቅስቃሴ ሃኪሞች የ20-20-20 ህግ (20-20-20 rule) ብለው ይጠሩታል፡፡ሌላው እንቅስቃሴ ደግሞ፡ ወደሩቅ ቦታ ከ10-15 ሴኮንዶች ይመልከቱ ከዛም አንድ ቅርብ ወዳለ እቃ አፍጥተው ለ 10-15 ሴኮንዶች ይመልከቱ በመቀጠል ወደሩቁ ቦታ ይመልከቱ፡፡ ይህንንም ለ10 ጊዜ ያህል ይደጋገሙ፡፡

5. መነጽር ያድርጉ ፡

በመጨረሻም ለተሻለ ምቾት የኮምፒዉተር ነጸብራቅን ለመከላል የተዘጋጀ መነጽርን መጠቀም ተገቢ ነው፡፡

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement