በእርግዝና ወራት የሚያጋጥመው የማቅለሽለሽ ስሜትና መፍትሄዎቹ!

                                                

በእርግዝና ወራት ሊከሰቱ ከሚችሉ ሁኔታዎች አንዱ ጠዋት ጠዋት ምቾት

ማጣት አንዱ ነው። በተለይ ማለዳ ላይ አብዛኛዎቹ ነፍሰጡሮች የማቅለሽለሽና
የማስመለስ ህመም ያጋጥማቸዋል። አብዛኞቹ ጠዋት ላይ ነው የሚያጋጥማቸው። ይህ ስሜት በአንዳንዶቹ ላይ ግን ቀኑን ሙሉና እስከ ምሽት ድረስ ሊዘልቅ ይችላል። በየትኛውም ጊዜ ላይ ቢከሰት ግን የነፍሰጡሮችን ስሜት
የሚረብሽ ነውና የቻሉት የራሳቸውን ዘዴ ተጠቅመው ችግሩን ለመቀነስ ይጥራሉ።ይህ አልሆን ሲላቸው ደግሞ የሀኪም እርዳታን ይጠይቃሉ። እኛም የሚከተሉት የመፍትሄ አቅጣጫዎች ይህን የህመም ስሜት ያስታግሳሉ በሚል አቅርበናል። 
1.በቂ እንቅልፍ መተኛት በምሽት ወደ መኝታ ቤት ስናመራ ከሚረብሹ ነገሮች መራቅ ይኖርብናል። በባዶ ሆድ ወደ መኝታ መሄድ ደግሞ ችግሩን ያብሳል፤ ጨጓራ በተራበ ስአት የሚረጨው አሲድ የማቅለሽለሽ ስሜትን ስለሚፈጥር። የመመገቢያና የመኝታ ስአትን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ማራራቅም ይመከራል።
2. የገብስ ቆሎና መሰል ቀላል ምግቦችን መመገብ በማለዳ የማቅለሽለሽ ስሜት ሲከሰት ተቻኩሎ ከአልጋ ከመነሳት ይልቅ እዚያው ጋደም እንዳሉ እንደ ገብስ ቆሎ ያሉ ለጨጓራ ቀለል ያሉ ምግቦችን መመገብ ያሻል።
3. ትንሽ ትንሽ ግን ቶሎ ቶሎ መመገብ የተቀቀለ እንቁላል፣ አይብ እና እርጎን
የመሳሰሉ በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ ተገቢ ነው። የተጠበሱና ቅባት
የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ ግን አይመከርም። 
4. ውሃ አብዝቶ መጠጣት
5. የሎሚ አልያም የዝንጅብል ሻይ መጠጣት የማቅለሽለሽ ስሜትን ይቀንሳል።
6. ሎሚ ማሽተትም በተመሳሳይ መልኩ የማቅለሽለሽ ስሜትን ይቀንሳል።

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement