የፊት ድርቀትን መከላከል

                                        

የፊት ድርቀትን መከላከልና ጥራቱን መጠበቅ የሚችሉባቸውን 5 መንገዶች 
1፡ዝኩኒ እና ማር
-1 ዝኩኒ በመፍጫ መፍጨት እና ከ 2 የሻይ ማንኪያ ማር ጋር መደባለቅ
-የተደባለቀውን ውህድ ፊቶት ላይ መቀባት
-እስኪደርቅ መጠበቅ ከዛም ለብ ባለ ውሃ መታጠብ

2፡የወይራ ዘይት
-ማታ ማታ ፊቶትን ከታጠቡ በኋላ በስሱ መቀባት

3፡ሙዝ፤እርጎ እና ማር
-1ሙዝ፤ሩብ ስኒ እርጎ እና 2 የሾርባ ማንኪያ ማር አንድ ላይ መደባለቅና ፊቶትን መቀባት
-ለ15ደቂቃ ፊቶት ላይ ማቆየት ከዛም በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ

4፡የገብስ ዱቄት፤እርጎ፤ማር እና እንቁላል
-ሩብ ስኒ የገብስ ዱቄት ውስጥ ግማሽ ስኒ ለብ ያለ ውሃ መጨመር
-ውህዱንም ለ5ደቂቃ ማቆየት
-ከዛም ያዘጋጀነውን ውህድ ከ2 የሾርባ ማንኪያ እርጎ፤2 የሾርባ ማንኪያ ማር እና ከ1 እንቁላል ጋር መደባለቅ
-ይህንንም ፊቶትን መቀባት እና ከ10-15ደቂቃ ማቆየት
-ለብ ባለ ውሃ መታጠብ

5.አቮካዶ እና ማር
-እኩል መጠን አቮካዶ እና ማር ማደባለቅ እና ለ20ደቂቃ ተቀብቶ ማቆየት
– ከዛም በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement