የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጥቅም

                                                 

ለካንሰርና እባጮች

አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከ አንድ የሻይ ማንኪያ የተፈጥሮ ማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ ግማሽ ሠዓት በፊት ይጠቀሙ።

• ለስኳር በሽታ
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከተፈጥሮ ማር ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። ካርቦሃይድሬት ያላቸውን ምግቦች በመጨመር ስኳርን በማቆም የአመጋገብ ለውጥ ያድርጉ።
• ለተቅማጥ
አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ኩባያ እርጎ ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ።
• ለደረቅ ሳል
ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከቡና ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። ጀርባዎና ደረትዎን በዘይት ይሹት።
• ለጆሮ ህመም
በስሱ የተቆላ አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ይውሰድ ከዚያም ጥቂት የኦሊቭ ዘይት ጠብታዎች በመጨመር በደንብ ይቀላቅሉት። ሰባት ጠብታ በሲሪንጅ ውስጥ ይክተቱ ከዚያም ጠዋት እና ማታ ጆሮዎ ውስጥ ይጨምሩ።
• ለዓይን ህመም እና ለእይታ ችግር
ወደ መኝታ ከመሄድዎ ከግማሽ ሠዓት በፊት የአይን ቆብዎን በጥቁር አዝሙድ ዘይት ይሹት። ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ኩባይ የካሮት ጭማቂ ጋር በመቀላቀል ይጠጡ።
• ለፊት ፓራሊሲስ
አንድ የሻይ ማንኪይ ዘይት ለብ ባለ ውሃ ውስጥ በመጨመር እንፋሎቱን ይታጠኑ።
• ለጉንፋን እና ፍሉ
አንድ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ በፊት ይውሰድ። በእያንዳንዳቸው የአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ጥቂት ጠብታዎች ይጨምሩበት።
• ለሃሞት ጠጠር እና ለጉበት ጠጠር
አንድ ትልቅ ማንኪያ የጥቁር አዝምድ ፍሬ ከማር ጋር በብርጭቆ ውስጥ ይቀላቅሉት ጥቂት ለብ ያለ ውሃ ይጨምሩበት። በመጨረሻም በመጨረሻም አንድ የሻይ ማንኪያ ዘይት ይጨምሩበት ይህን ውህድ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ይጠጡ።
• ለአጠቃላይ ጤንነትና ደህንነት
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከአንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል በየቀኑ ይጠቀሙ። ወይም ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ዘይት ከማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ በፊት በየቀኑ ይጠቀሙ።
• ለፀጉር መሳሳት እና ያለ ዕድሜ ሽበት
በመጀመሪያ ፀጉርዎን ይታጠቡ ከዚያም በቂ የሆነ የኦሊቭ ዘይት ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር በመቀላቀል ይቀቡት። ከአንድ ሠዓት ቆይታ በኋላ ያለቅልቁት ወይም ይታጠቡት።
• ለራስ ህመም እና ማይግሬን
ከግንባርዎ ግራ ክፍል ትንሽ ዝቅ ብሎ ወይም ቴምፕል በሚባለው የጥቁር አዝሙድ ዘይት በመቀባት ይሹት። ጥቂት ጠብታዎች በአፍንጫዎ ቀዳዳ እና ጭንቅላትዎ ላይ ያድርጉ። በቀን ሁለት ጊዜ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬና ማር ይብሉ።
• ለማስታወስ ችሎታ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል በቀን ሶስት ጊዜ ይመገቡ።
• ለአፍ ኢንፌክሽን ቫይረስ
ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬ በአፍዎ ውስጥ ከ 10 – 15 ደቂቃ ይያዙት።
• ለጡንቻ ህመም
አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ከማር ጋር በመቀላቀል በቀን ለሶስት ጊዜ ይውሰድ። የቅልጥም መረቅ በየቀኑ ይጠጡ። የቻሉትን ያክል ዘቢብ በየቀኑ ይመገቡ።
• ለሪህና ጀርባ ህመም
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ሞቅ በማድረግ የሚያምዎትን ቦታ ይሹት። በየቀኑ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ እና ማር ይመገቡ።
• ለሆድ ህመም
በአንድ ትልቅ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከማር ጋር በመቀላቀል ይጠቀሙ። ጥቂት የፔፐርሜንት ሻይ ይጠጡ ከዚያም የረሃብ ስሜት ከተሰማዎት የተቀቀለ ሩዝ ውሃ ይጠጡ።
• ለጥርስ ህመምና ድድ ኢንፌክሽን
በኩባያ የሎሚ ጭማቂ በማድረግ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ይጨምሩበት ከዚያም ያፍሉት። ከዚያም የፈላው ሎሚ ቀዝቀዝ ሲል በዚህ ውህድ ፈሳሽ አፍዎን ይጉመጥመጡበት/ይታጠቡበት።
• ለሆድ ትላትል
ሁለት የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከግማሽ ኩባያ ሎሚ ጋር በመቀላቀል ይህን ውህድ ያሙቁት። ከዚያም ቡርሽ ወይም ሌላ ነገር በመጠቀም የሆድና ጉበትዎን አካባቢ ይሹት።

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement