መካንነት ማለት ቢያንስ ለአንድ አመት ያህል ሙከራ አድርገው ለማርገዝ አለመቻል ነው። ማርገዝ የምትችል ሴት ነገር ግን ሳትወልድ በመደበኛ ሁኔታ መጨንገፍ እንደ መካንነት ይቆጠራል።
✔ በእርግዝና ወቅት የሚከተሉት ሂደቶች መከናወን አለባቸው፦
※ ሴቷ ከእንቁልጢ (የእንቁላል ከረጢት) እንቁላል መልቀቅ አለባት።
※ እንቁላል በማህፀን ቱቦ አማካይነት ወደ ማህፀን መጓዝ አለበት።
※ የወንድ የዘር ፍሬ ሴት እንቁላል ውስጥ መግባትና ውህድ ህዋስ መፍጠር አለበት።
※ ውህድ ህዋሱ (fertilized egg) በማህፀን ውስጥ መጣበቅ አለበት። ይህም ትክለት ወይም ጥባቄ ፅንስ (Implantation) ይባላል። መካንነት ከነዚህ ከላይ ከተዘረዘሩት ሂደቶች አንድ ሲስተጓጐል ይከሰታል።
✔ መካንነት የሴቶች ችግር ብቻ ነው?
※ መካንነት ወንድና ሴትን የሚያጠቃ ሲሆን ሁለቱም ፆታዎች ላይ በእኩልነት ይከሰታል።
※ የወንድ የዘር ፍሬ ቁጥር መቀነስ፣ የብልት ከተለመደው ውጭ መሆን (ችግር) እና የስሜት ጣሪያ ላይ ለመድረስ መቸገር የተለመድ የወንድ መካንነት መነሾ ምክንያቶች ናቸው።
※ በጣም የተለመድ በሴቶች ላይ የሚከሰት መካንነት መነሾዎች መካከል፦ ኢንዶሜትሪዮሲስ፣ ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም እና የመውለጃ ዕድሜ ከፍ ማለት የእንቁላል ብዛትና ጥራትን ይቀንሰዋል።
✔የመካንነት ምልክቶች!
በመደበኛ ሁኔታ ያልተጠበቀ ወይም ያልተገደበ የግብረ ስጋ ግንኙነት እንደ ዕድሜዎ ሁኔታ ከ ስድስት (6) ወር እስከ አንድ ዓመት አድርገው እርግዝና ያልተከሰተ እንደሆነ መካንነት እንለዋለን። ዋናው የመካንነት ምልክት አለማርገዝ (ለማርገዝ መቸገር) አይደለም። ምልክቶቹ እንደ መካንነቱ መነሾ ምክንያት ይወሰናል አንዳንድ ጊዜ መነሾው ላይታወቅ ይችላል።
✔ የመካንነት ምልክቶች በሴቶች!
የወር አበባ ኡደት መቀየር ወይም የሴት ዘር መፈልፈል ከመካንነት ጋር ሊያያዝ ይችላል። ይህም የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
※ የተዛባ የወር አበባ
※ ከመደበኛ ሁኔታ ውጪ የሆነ የወር አበባ ይህ ማለት የወር አበባ ከመጠን በላይ መፍሰስ ወይም በጣም ትንሽ መፍሰስ ነው።
※ የወር አበባ ከሌለ ይህ ማለት የወር አበባዎ በድንገት ከቆመ ወይም ከነጭራሹ ካልመጣ ነው።
※ ከባድ ህመም ያለው የወር አበባ።
የመካንነት ችግር በተጨማሪ ከሆርሞኖች ጋር ሊያያዝ ይችላል ታዲያ በዚህ ጊዜ የሚከተሉት ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ ከነዚህም መካከል፦
※ የወሲብ ፍላጐት መለወጥ/መቀየር።
※ በቆዳ ላይ የሚታዮ ለውጦች ለምሳሌ ብጉር።
※ የፀጉር መሳሳት ወይም መመለጥ።
※ የሰውነት ክብደት መጨመር።
※ በጭን፣ ደረትና ከንፈር አካባቢዎች ጥቁር ፀጉር ማብቀል ናቸው።
በተጨማሪም በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ከፍተኛ ህመም እና ከጡት ጫፍ ነጭ ወተት መሳይ ፈሳሽ መውጣት ዓይነት ምልክቶች ሊታዮ ይችላሉ።
✔ የመካንነት ምልክቶች በወንዶች ላይ!
መካንነት በወንዶች ላይ ልጅ ለመውለድ እስካልሞከሩ ድረስ ምንም ላይታወቅ ይችላል። ምልክቶቹ የመካንነት መነሻ ምክንያቶቹ ላይ ይወሰናል ከነዚህ ምልክቶች መካከል፦
※ የወሲብ ፍላጐት መቀያየር ወይም መለዋወጥ።
※ የብልት መቆም እና መርጨት ቸግር።
※ የብልት ህመም፣ መጓጐል ወይም ላብ (ማላብ)።
※ የፀጉር ዕድገት ለውጥ።
※ ትንሽና የጠበቀ ብልት ናቸው።
✔ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያለብን መቸ ነው?
※ ዕድሜያቸው ከ 35 ዓመት በታች ከሆነና ለማርገዝ ወይም ጽንስ ለመቋጠር ለአንድ ዓመት ያህል ሙከራ ካደረጉና ካልተሳካ።
※ ዕድሜያቸው ከ 35 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሴቶች ለስድስት(6) ወር ያህል ሙከራ ካደረጉ በኋላ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ሀኪምዎን ያማክሩ።
ምንጭ:- ጤናችን