የሳንባ ምች – Pneumonia

                                          

የሣንባ ምች እንዴት ይከሰታል?

 በባክቴሪያ
 በቫይረስ
 በሽታን የመከላከል አቅማቸው የደከመ ሰዎች ላይ ይከሰታል
አንድ ሰው አየር በሚያስገባ ጊዜ እነዚህን በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ወደ ውስጥ ያስገባል፡፡ይህም ወደ ሣንባ በመሄድ ኢንፌክሽን ይፈጥራል፡፡

ለሣንባ ምች ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች
 ዕድሜ፡-ዕድሜያቸው ከ1 ዓመት በታች የሆኑ እና ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ ሰዎች
 በሽታን የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች
 በጉንፋን የተጠቁ ሰዎች
 የአስም ሕመም ተጠቂ የሆኑ ሰዎች
 ሲጋራን ማጤስ
 የአልኮል መጠጥን እጅግ ማዘውተር

የሣንባ ምች ሕመም ምልክቶች
 አክታ የተቀላቀለ ሳል
 ትኩሳት
 ትንፋሽ ማጠር
 የራስ ምታት
 ብርድ ብርድ ማለት
 የደረት ውጋት በሳል ጊዜ የሚብስ
 የልብ ትርታ መጨመር
 ላብ ላብ ማለት
 የሰውነት ድካም
 የምግብ ፍላጎት መቀነስ
 ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ

የሣንባ ምችን እንዴት መከላከል ይቻላል?
 ሲጋራ ማጤስን ማቆም
 እጅን በሚገባ መታጠብ

የሣንባ ምችን ሕምተኞች በቤት ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚችላቸው ሕክምናዎች፤
 ፈሳሽ በብዛት መውሰድ
 ዕረፍት ማድርግ
 ትኩሳትን ማስታገሻ በመውሰድ መቆጣጠር
 ነጭ ሽንኩርትን መመገብ

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement