10 የኩላለት በሽታ ምልክቶች

 የሽንት ስርዓት መዛባት/መቀየር

የመጀመሪያው የኩላሊት በሽታ ምልክት የሽንት ሥርዓት መለወጥ ነው፡፡ መለወጥ ስንል የሽንት መጠን እና ሽንትዎን የሚሸኑበት የጊዜ ልዩነት ነው፡፡ ሌሎች ለውጦች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦

ሌሊት ሽንት ለመሽናት ደጋግመው መነሳት

ለመሽናት መቸኮል

ከተለመደው ጠቆር ያለ ሽንት

አረፋ ያለው ሽንት

ደም የተቀላቀለበት ሽንት

ሲሸኑ መቸገር/በጣም መግፋት ለመሽናት

በሚሸኑበት ጊዜ ህመም ወይም የማቃጠል ስሜት

የሰውነት እብጠት

ተረፈ ምርቶችንና ትርፍ ፈሳሾችን ከሰውነታችን ማስወገድ የኩላሊት ስራ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ሲሳነው ግን የትርፍ ፈሳሽና ውሃ መከማቸት እብጠት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ እነዚህ እብጠቶች በእጅ፣ እግር፣ ቁርጭምጭሚት መገጣጠሚያ፣ ፊት እና አይን አካባቢ ይፈጠራሉ፡፡

 

ከፍተኛ የሆነ የመዛልና የድካም ስሜት

ኩላሊት ተግባሯን በትክክል መወጣት በሚያቅታት ወቅት አብዛኛውን ጊዜ የመዛል ስሜት ይሰማናል፡፡ ይደክምዎታል ወይም በአጠቃላይ ባላወቁት ምክንያት ሃይል/ጉልበት ያጥርዎታል፡፡ የዚህ ምልክት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች የደም ማነስና በሰውነት ውስጥ የተረፈ ምርቶች/ቆሻሻዎች መከማቸት ነው፡፡

 

የማዞር ስሜት

በኩላሊት በሽታ ምክንያት የደም ማነስ የሚከሰት ከሆነ በተደጋጋሚ ያዞርዎታል የዚህም ችግር የራስ መቅለል፣ ባላንስ ማጣት ዓይነት ስሜቶች/ምልክቶች ይታይብዎታል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የደም መነስ በሽታው ወደ አእምሮ በቂ የሆነ ኦክስጂን እንዳይደርስ ስለሚያደርግ ነው፡፡

 

የጀርባ ህመም

ይህ ነው የማይባል የህመም ስሜት በጀርባዎና በሆድዎ ጎንና ጎን መሰማት የኩላሊት በሽታ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ኩላሊት በትክክል ስራውን መስራት ካልቻለች የመገጣጠሚያ ህመም፣ መገተር/ለማጠፍ መቸገርና ፈሳሽ ይስተዋላል፡፡

 

የቆዳ መሰነጣጠቅና ማሳከክ

ድንገተኛ የሆነ የቆዳ መሰነጣጠቅ፣ ሽፍታ፣ ማቃጠል/መለብለብ እና ከፍተኛ የማሳከክ ስሜት ተጨማሪ የኩላሊት ችግር ምልክቶች ናቸው፡፡ ኩላሊት ተግባሩን በትክክል አለመወጣት ቆሻሻዎችና መርዛማ ነገሮች በሰውነት ውስጥ እንዲከማቹ አስተዋጽዎ ስለሚያደርግ በርከት ላሉ የቆዳ ችግሮች ያጋልጣል፡፡

 

የአፍ ሽታ

የኩላሊት በሽታ የአፋችን ጣዕም ብረት ብረት እንዲለን ወይም አፋችን የአሞኒያ(የሽንት) ሽታ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ይህ የሚሆነው ደካማ የሆነ የኩላሊት ተግባር በደም ውስጥ ያለው የዩሪያ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ዩሪያ በምራቅ በመሰባበር ወደ አሞኒያ ይቀየራል ይህም አፋችን መጥፎ የሆነ ሽንት የሚመስል ሽታ እንዲኖረው አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

 

ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ

በኩላሊት በሽታ የሚሰቃዩ ሰዎች ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ በጣም የተለመዱ ምልክቶች ናቸው፡፡ የማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ስሜት በአብዛኛው የሚኖረው ጠዋት ከእንቅልፍዎ በሚነሱበት ወቅት ነው፡፡

 

አብዛኛውን ጊዜ ይበርድዎታል

ይህ በኩላሊት በሽታ ምክንያት በተፈጠረ ደም ማነስ ምልክት ነው፡፡ በማያውቁት ምክንያት የብርድ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል ምንም አየሩ ሙቀት ቢሆንም እንኳን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ከማዞርና ድካም በተጨማሪ የሚበርድዎት ከሆነ በፍጥነት ህክምና ያግኙ፡፡

 

የትንፋሽ ማጠር

የትንፋሽ እጥረት የኩላሊት በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ኩላሊት ተግባሯን በትክክል አለመወጣቷ በሳንባ ውስጥ በዛ ያለ ፈሳሽ እንዲከማች ያደርጋል፡፡ ይህ የትንፋሽ ማጠር በኩላሊት ችግር ምክንያት በተፈጠረ የደም ማነስ ሊሆን ይችላል፡፡

 

 

Advertisement