SPORT: አሌክሳንደር ላካዜቲ በይፋ አርሰናልን ተቀላቀለ::

                         

አሁን ጥያቄው ከ 2004 አንስቶ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ በናፈቀው አርሰናል ውስጥ ፈረንሳዊው አጥቂ ልዩነት መፍጠር ይችላል ወይ? ወይም ደግሞ በሌላ ቋንቋ ልዩነት ለመፍጠር የሚችል ጥራት ያለው አጥቂ ነው ወይ? የሚለው ሆኗል። 

አርሰናል ሮቨን ቫምፐርሲን ለዩናይትድ አሳልፎ ከሰጠ ወዲህ ለትንሽ ጊዜያት የፊት አጥቂ ሲያፈላልግ ቆይቶ የሞንቴፕሌዩን ኦሊቬ ዢሩን አስፈርሟል። በእርግጥ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በ9 ቁጥር ሚና ላይ አሌክሲስ ሳንቼዝ የተጫወተባቸው ጊዜያት አሉ። በመጨረሻ ግን ቬንገር ወደ ኮሪደር ወጥቶ እንዲጫወት ስለሚፈልጉ ወደቦታው መልሰውታል። የቡድኑ የፊት መስመር መሪ በአብዛኛው ጀዢሩ ነበረ።

ጂሩድ ለደጋፊዎች ተስፋ መቁረጥ መስበሪያና በአንዳንድ ወቅቶች ላይ አስደናቂ ብቃቶችን ማሳየት የሚችል አጥቂ ነው። ለዚህ ደግሞ በክሪስታል ፓላስ ላይ በጊንጥ (ስኮርፒዮን) ቅንጡ የአመታት ስልት ያስቆጠራት ግብ እንዲሁም ደግሞ ሚያዚያ 2014 ባማረ ንክኪ ዌስትሀም መረብ ላይ ያሳረፋትን ግብ መመልከት በቂ ነው። 

ነገርግን ጂሩድ አርሰናልን የእንግሊዝ ምርጡ ቡድን ለማድረግ የሚችል የአለም ኮከብ አጥቂ ደረጃ ላይ ያለ ተጫዋች አይደለም። ላከዜቲስ ይህን ችግር የሚቀርፍ ጥራት ያለው አጥቂ ነውን? ቬንገር በዢሩ እንደማይተማመኑ ከዚህ ቀደም ፈረንሳዊው በኢምሬትስ አንደኛ አመቱን ባከበረበት ወቅት ሊውስ ስዋሬዝን ለማስፈረም በመሞከር አሳይተዋል። ሳንቼዝን ቦታ በመቀየር በፊት አጥቂነት የሞከሩበት ተግባርም አንዱ ማሳያ ነው። አሁን ደግሞ የሊዮኑን አጥቂ አምጥተው በዢሩ እንደማይተማመኑ በተግባር አሳይተውታል።

አስደናቂው ነገር ዢሩድ የአንቶኒ ግሪዝማን ረዳት በሆነበት በዲዲየር ዴሻይ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ ላካዜቲ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ለመግባት ቀርቦ አያውቅም። ሰኔ ሶስት ቀን ከፖራጓይ ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ ሀትሪክ በሰራው ዢሩድ ተቀይሮ ወደሜዳ ሲገባም ከጥቅምት 2015 በኋላ የፈረንሳይን ማሊያ ያጠለቀበት የመጀመሪያ ጊዜ ነበር። 

ዴሻምይ ለቀድሞው የሊዮን አጥቂ 2013 ላይ ከፖራጓይ ጋር በነበረው ጨዋታ የመሰለፍ እድል ቢሰጠውም በቋሚነት ሊያሰልፈው የቻለው ግን በ 11 ጨዋታዎች ላይ ብቻ ሲሆን ዢሩድ የቡድኑ ቁልፍ ሰው በነበረባቸው የ 2014 አለም ዋንጫና የ 2016 አውሮፓ ዋንጫ ላካዜቲ በቡድኑ አልነበረም። 

ዴሻምፕ ግን ዢሩድን መምረጡ ላካዜቲን ያልፈለገ የሚመስል ስሜት መፍጠር እንደሌለበት ይናገራል። ሁለቱ ተጫዋቾች የተለያየ ባህሪ ያላቸው የ9 ቁጥር ተሰላፊዎች ናቸው። ጂሩድ የተለመደው አይነት የፊት መስመር ተጫዋች ሲሆን ላካዜቲ በበኩሉ ተንቀሳቃሽ ተጫዋች ነው። ለቡድኑ ሚዛን መጠበቅ ሲልም ዴሻምፕ ዢሩድን ይመርጣል።

ከዚህ በተጨማሪም ዴሻምፕ ብዙ አማራጭ የፊት መስመር ተጫዋቾች አሉት። በዛ ላይ ደግሞ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድኑ አለቃ ላካዜቲ ቋሚ ከሚሆን ይልቅ በተቀያሪነት ቢገባ የተሻለ ተፅዕኖ ያሳድራል የሚል አስተሳሰብ ሊኖረው እንደሚችል ይጠበቃል። 

ላካዜቲ ባለፉት ሶስት አመታት በፈረንሳይ ሊግ አንድ ድንቅ ብቃት አሳይቷል። በሊዮን ቤት የሚገኙ አንዳንዶች ግን የእሱ ትልቁ ብቃት የታየው በ 2014-15 ከናቢል ፊኪር ጋር ባሳየው ጥምረት እንደሆነ ይናገራሉ። በዛ ወቅት ላካዜቲ የእግር ኳስ ችሎታውን ባሳደገበትና የሰዎችን ቀልብ በገዛበት የውድድር ዘመን በ 31 የሊግ ጨዋታዎች 27 ጎሎችን አስቆጥሮ ነበር። 

ከዛም ቁጥሮቹ እድገታቸውን ቀጥለው በ 30 ጨዋታዎች ላይ 28 ጎሎችን በሁሉም ውድድሮች ላይ ባደረገው 45 ጨዋታ ላይ ደግሞ 37 ግቦችን አስቆጠረ። ከዚህ ቀደም በትልልቅ ጨዋታዎች ላይ የሚጠበቅበትን አላሳየም ተብሎ ሲተች የነበረው አጥቂ እራሱን ለትልቅ ተጫዋችነት አበቃ። 

ቬንገርም በተጨዋቹ ብቃት አምነው ነበር። በአመቱ መጨረሻ ፈረንሳይ ከፓራጓይ፣ ስዊድንና እንግሊዝ ጋር በነበራት ጨዋታ ላይም ላካዜቲ እራሱን በትልቅ ደረጃ የሚያሳይበት እንደሚሆን ተጠበቀ።  ነገርግን ዴሻምፕ ትልልቅ ስም ያላቸውን ተጫዋቾች ማሰለፍ በመፈለጉ ላካዜቲን በቋሚነት ሳያሰልፍ ዘለለው። ይህ ሁኔታም የተጫዋቹን የዝውውር ሁኔታ ረበሸው።

በመጨረሻ ግን ከክንፍ ተጫዋችነት ሚና ቀይሮ በፊት አጥቂነት ትልቅ ተፅዕኖ ማሳደር የቻለው በኳስ አገፋፍ፣ በስኬት መጠኑ፣ በጠንካራ ሰራተኛነቱ፣ በፍጥነቱና በቴክኒካል ብቃቱ እንዲሁም በጎል አነፍናፊነቱ የተለየውን አጥቂ አርሰናል በእጁ ማስገባት ችሏል። ላካዜቲ በአያን ራይት የተለመደውን በአንድ ሁለት ቅብብል የጎል ሳጥን ውስጥ መግባትን ይወዳል። ከዢሩድ የበለጠ ተንቀሳቃሽ በመሆኑ ባሳለፍነው ሚያዚያ በቬንገር ለተተገበረው የ 3-4-2-1 ሆነ የ 4-2-3-1 እና 4-3-3 አሰላለፍ መሆን የሚችል ተጫዋች ነው። 

በሌላ በኩል ግን የላካዜቲ ተቺዎች ፈረንሳዊው አጥቂ የአለም ኮከብ አጥቂ የመሆን ብቃት ቢኖረው ኖሮ ሊዮንን የሚለቀው ከሁለት እና ሶስት አመታት በፊት እንደሆነ በመግለፅ ያስቆጠራቸው ግቦች ብዙ ፍፁም ቅጣት ምቶች ይበዙዋቸዋል ሲሉ ይከራከራሉ

ምንጭ-ኢትዮአዲስስፖርት

Advertisement