ስርቅታ(ስቅታ) ምንድን ነው? እንዴት ልንከላከለው እንችላለን? – What is Hiccups And How can We Prevent It?

                                         

ስርቅታ ድንገተኛ ያለውዴታ ወይም ሳያዙት ከቁጥጥር ውጪ የዲያፍራም ጡንቻዎች መጨማደድ/መሰብሰብ ሲሆን የነዚህ ጡንቻዎች መሰብሰብ የድምጽ አውታሮች ይዘጉና የስርቅታ ድምጽ ይፈጠራል። ዲያፍራም(በሆድና ሳንባ መሀል የሚገኝ ጡንቻ) ተጨማዶ ስርቅታ እንዲፈጠር ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል:- ሆዳችን በምግብ ሲወጠር/ሲለጠጥ፣ አልኮል፣ አየር፣ የጨጓራ የሙቀት መጠን ሲቀየር፣ አልኮል/ሲጋራ በብዛት ስንጠቀም ይፈጠራል ማለት ነው። በተጨማሪም ስንሸበር ወይም በጣም ሲደክመን ይከሰታል።

በአብዛኛው ስርቅታ ከጀመረን በኃላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚቆም ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ለቀናቶችና ሳምንታቶች ሊቆይ ይችላል ይህ ያልተለመደ ሲሆን ሌላ በሽታዎች እንዳሉብን አመላካች ነው። ከእነዚህ በሽተዎች መካከል በዲያፍራም አካባቢ መርፌ ወይም በሌላ ስለት ነገር መወጋት፣ የአንጀት መውረድ፣ ብርቱ ከጉሮሮ እስከ አንጀት ባሉ የሰውነት ክፍሎች ህመም እና በደረት ነርቮች መቆጣት ምክንያት የሚፈጠሩ እጢዎች ናቸው። ከአንድ ወር በላይ የሚቆይ ስርቅታ በህክምና የማይድን ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልዋል።

ወደ ህክምና መስጫ ተቋም መሄድ የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ካሉ ከታች ከተዘረዘሩት አንድን ቀላል መንገድ መጠቀም ተገቢ ነው።
1.በወረቀት ቦርሳ/ከረጢት ውስጥ መተንፈስ
2. ከአፍዎ በተቃራኒ ካለው የብርጭቆ ጠርዝ ላይ ለመጠጣት መሞከር
3. ትንፋሽዎን ቆጥበው ሳይተነፍሱ ለትንሽ ጊዜ መቆየት
4. ሎሚ መምጠጥ
5. ስኳር መቃም
6. ጆሮዎን በጣትዎ ደፍነው በስትሮው(straw) ውሀ መጠጣት
7. የፀጉርዎን ጫፍ ይዘው ለ1 ወይም ሁለት ደቂቃ ወደላይ መሳብ
8. በውሀ በተነከረ ጥጥ ላንቃችንን ማሸት/መጥረግ
9. ምላስዎን ወደ ውጪ ቀጥ አድርገዉ መሳብ

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement