ካንሰርን የሚለይ ማስቲካ ተሰርቷል – Cancer Detecting Chewing Gum.

                                                              

አንድ ሰው በካንሰር መያዝ አለመያዙን ለማወቅ የደም፣ የሽንት እና ሌሎች ምርመራዎችን ማድረግ የግድ ነው።

አሁን ላይ ግን ይህንን ሊያስቀር የሚችል አዲስ የመመርመሪያ ዘዴ አግኝተናል ይሉናል ተመራማሪዎች።

አዲሱ ዘዴያቸውም የሚታኘክ ማስቲካ ሲሆን፥ የታኘከው ማስቲካም በካንሰር መያዛችንን እና አለመያዛችንን በቀላሉ ለመለየት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ማስቲካውን በምናኝክበት ጊዜም ማስቲካው በምራቃችን ውስጥ የሚገኘውን እና በተለያዩ አይነት ካንሰሮች የሚለቀቀውን የኬሚካል ኮምፓውንድ የያዘውን “ቮላታይል” አንድ ላይ መጦ ይይዛል።

ማስቲካው ለ15 ደቂቃ ከታኘከ በኋላ እነዚህን ኬሚካሎችን በውስጡ መያዝ አለመያዙ ይታያል ተብሏል።

በአሜሪካ አላባማ የሚገኙት ተመራማሪዎች እንዳስታወቁት፥ ለምርመራው የተለያዩ አይነት ማስቲካዎች ተሰርተዋል።

ማስቲካዎቹም የጣፊያ፣ የሳንባ እና የጡት ካንሰርን ቀድሞ ለመለየት የሚያስችሉ መሆናቸውን ነው የሚናገሩት።

አሁን በማስቲካዎቹ ላይ እየተደረገ ያለው ሙከራ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ ከሆነም፥ ከዚህ በፊት ካንሰርን ለመመርመር ይደረግ የነበረውን የደም፣ የሽን እና ሌሎች አካላዊ ምርመራዎችን ሊያስቀር እንደሚችል ነው ተመራማሪዎቹ የተናገሩት።

ማስቲካውንም በቀጣዩ ዓመት ዶክተሮች እና ታካሚዎች ዘንድ እንዲደርስ ለማድረግ እንደሚሰሩ ያስታወቁ ሲሆን፥ ከካንሰር በተጨማሪም እንደ ቲቢ ያሉ ሌሎች ህመሞችን ለመለየት እንደሚያስችሉ ተስፋ አደርገዋል።

በአሁኑ ጊዜም በማስቲካው ጣእም ላይ እየሰሩ መሆኑን ያስታወቁት ተመራማሪዎቹ፥ ታካሚዎች የማስቲካውን ጣእም እና ቃና እንዲወዱ የሚያደርጉ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች እንደሚካተቱበትም አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk

Advertisement